በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ታላቁ የ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ታላቁ የተራራ ላይ የእግር ጉዞ ውድድር ተካሄደ

በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ታላቁ የተራራ ላይ የእግር ጉዞ ውድድር ተካሄደ

ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከማስተር ሄኖክ 90 ቀናት ለሁለንተናዊ ለውጥ ማዕከል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የ5 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ ውድድር ክብር ፍቅርና ሕብር በሚል መሪ ቃል በእንጦጦ ፓርክ ተካሄደ

መነሻና መድረሻውን እንጦጦ ፓርክ በማድረግ በተካሄደው የእግር ጉዞ ላይ ከ10ሺ በላይ ነዋሪዎች ከመሳተፋቸው ባሻገር አሳታፊና አዝናኝ የስፓርት ውድድሮች ጨምሮ ልዩ ፌስቲቫሎች መካሄዳቸው ተመልክቷል

እንደ ከተማ አስተዳደር ከተሰሩ አንዱ በሆነው የቱሪዝም መዳረሻ የተካሄደው የእግር ጉዞ ጤናን በመጠበቅ የእርስ በእርስ ትስስርን ያጠናክራል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልድሃና ዝግጅቱ በፈጣን ዕድገት ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ይበልጥ ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ ገልጸዋል

በርካታ ነዋሪዎች የተሳተፉበት በአይነቱ እና በይዘቱ ልዩ የሆነው ሃይኪንግ ለስፓርቱ መነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ማንኛውም ዜጋ በሚኖርበት፣ በሚሰራበት፣ በሚማርበትና በሚዝናናበት አከባቢ ስፖርት ለማስፋፋት ከሚሰሩ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል

ቢሮው ከሄኖክ ኪዳነወልድ ሰልጠናዎች ጋር በጋራ ለመስራት የሁለትዮሽ ስምምነት ካደረገ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን የገለጹት አቶ ዳዊት ዓለም አቀፍ የቱሪስ መዳረሻ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ በተሰራው እንጦጦ ፓርክ የተካሄደው የእግር ጉዞ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል

የ90 ቀናት ሁለንታነዊ ለውጥ ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ ማስተር ሔኖክ ኪዳወልድ በበኩላቸው በርካታ ሰዎችን በማሳተፍ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ጀግና ትውልድ የተራራ ጉዞ

አዋቂዎች እና ህጻናት መሳተፋቸውን ገልጸው የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ዘርፍ ለማበረታታት እንደዚህ አይነት በፈጠራ የታጀቡ ተግባራት ወሳኝ መሆናቸውን አመልክተዋል

ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ቁጥሩ ትንሽ ቢሆንም ሃይኪንግ ውድድር ሲካሄድ መቆየቱን ያስታወሱት ማስተር ሔኖክ የዜጎች ሁለንተናዊ ጤንነት ለመጠበቅ እና ስፖርትን ባህል ለማድረግ የተራራ ላይ የእግር ጉዞ በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ በየ3 ወሩ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል

ማራኪ ገጽታ ነፋሻማ አየር መሰረተ ልማቶች በተሟሉለት እና የ14 ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው አሰፓልት መንገድ ባለው ፓርክ ለተደረገው ሃይኪንግ ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊው ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት እና ለውድድሩ አሸናፊዎች እውቅና ተሰጥቷል

የእግር ጉዞና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር ደስተኛ ለመሆን፣ ተጨማሪ ሃይል ለማግኘት፣ ለቆዳ ጤንነት፣ ለአዕምሮ ጤና፣ማስታወስ ችሎታ ለማዳበር፣ ለአዕምሮ ንቃት፣ በራስ መተማመንን ለማሳደግ የሰውነት የክብደት መጠንን ለመቀነስ ለጡንቻ እና ለአጥንት ጥንካሬ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በመድረኩ ተገልጽዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.