
ቢሮው ከልልምድ ቡኃላ የሚያካሂደው ምገባ ለታዳጊ ስፓርተኞች ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ
ቢሮው ከልልምድ ቡኃላ የሚያካሂደው ምገባ ለታዳጊ ስፓርተኞች ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ
ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር እያካሄደ የሚገኘው ታዳጊ ወጣቶች ከልምድ ቡኃላ ምገባ ለስፓርት ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ
በራስ ኃይሉ ስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘውን ምገባ የቢሮ አመራሮች ፣ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የመስክ ምልከታ የተካሄደ ሲሆን የስፓርተኞችን አመጋገብ በሳይንሳዊ መንገድ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑ ተመልክቷል
በልዩ ስልጠና ጣቢያ ለሚሰለጥኑ ታዳጊዎች የሚሰጠው ምገባ ተተኪ ስፓርተኞችን በብዛት እና በጥራት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ ገልጸዋል
ቢሮው የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር በመክፈት በ20 የስፖርት አይነት ከ20ሺህ በላይ ታዳጊዎችን በማስልጠን ላይ እንደሚገኝ ያስታወሱት አቶ ጎሳዬ በመስክ ምልከታው በልዩ ስልጠና ጣቢያዎች ለሚሰለጥኑ ታዳጊዎች አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት መኖሩን አመልክተዋል
በልዩ ስልጠና ጣቢያ የሚሰለጥኑ ታዳጊ ስፓርተኞች ተመጣጣኝ ምግብ አግኝተው በአካላቸው ብቁ በአዕምሮው ንቁ ሆነው እንዲያድጉ የምገባ ሥርዓቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመልክቷል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.