
በታዎቂ ሰዎች ስፖርት ፌስቲቫል የጋዜጠኞች ቡድን ሻምፒዮና ሆነ ሚያዚያ 26 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በታዎቂ ሰዎች ስፖርት ፌስቲቫል የጋዜጠኞች ቡድን ሻምፒዮና ሆነ
ሚያዚያ 26 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የቅዳሜ ሚዲያ እና አድቨርታይዚንግ በጋራ ባዘጋጁት የታዎቂ ሰዎች ስፖርት ፌስቲቫል የጋዜጠኞች ቡድን ድምፃዋያንን በመለያ ምት በማሸነፍ ሻምፒዮና መሆን ችሏል።
የጋዜጠኞች ቡድን የውድድሩ ሻምፒዮና በመሆን የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳልያ ሽልማት ሲበረከትለት ውድድሩን በሁለተኝነት ያጠናቀቀው የድምፃውያን ቡድን የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል።
በደረጃ በተካሄደ ጨዋታ አርቲስቶች ቲክቶከሮችን በጨዋታ 3 ለ1 በሆነው ውጤት በማሸነፍ የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሲሆኑ ቲክቶከሮች በአጠቃላይ በውድድሩ ባሳዩት ስፖርታዊ ጨዋነት የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ተገንብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ክፍት የተደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ለማስተዋወቅ ታሳቢ ያደረገው የታዎቂ ሰዎች ፌስቲቫል በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኝው ብሪሞ ሜዳ የተካሄደ ሲሆን ታዎቂ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ድምፃውያን እና ቲክቶከሮች በፌስቲቫሉ ተሳትፈውበታል።
ለሁለት ቀናት በተካሄደው ስፖርት ፌስቲቫል በእግር ኳስ ጋዜጠኛ ሰይድ ኪያር የአጠቃላይ የጨዋታው ኮከብ ተጨዋች ሆኗ ሲመረጥ አርቲስት ነብዩ እንድሪስ ከፍፃሜ ጨዋታ ቀደም ብሎ ለተካሄደው የደረጃ ጨዋታ ኮከብ ተጨዋች ተብሏ ተመርጧል።
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
43Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 41 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.