ፋይዳ ለኢትዮጵያ 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ፋይዳ ለኢትዮጵያ 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ግንባት 3 ይካሄዳል።

ፋይዳ ለኢትዮጵያ 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ግንባት 3 ይካሄዳል።

ሚያዚያ 28 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ፣ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ አገልግሎት አጄንሲ በጋራ የሚያዘጋጁት 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

ሶስቱ ተቋማት ዛሬ በአዳዲስ አበባ ከተማ ሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጎዳና ላይ ሩጫው ፋይዳ ለኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን ከ25ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፋበት መሆኑን ገልፀዋል።

በጋዛጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ስፖርት ጤናን ከመጠበቅ ባለፈ ማህበራዊ መስተጋብርን በመፍጠር አንድነት፣ አብሮነት፣ ወዳጅነት ለማጠናከር አስተዋፅኦው ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ፋይዳ ለኢትዮጵያ 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

መነሻውን እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በሚያደርገው የጎዳና ላይ ሩጫ አካል ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው የህብረተሰቦችን ጨምሮ ታዎቂ አቶሌቶች፣ አርቲስቶች፣ ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና የከተማው ነዋሪዎች እንደሚሳተፋ የገለፁት አቶ በላይ ከአንድኛ እስከ ሶስተኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ሽልማት እና ለአጠቃላይ ውድድሩን ለጨረሱ ተወዳዳሪዎች የሜዳልያ ሽልማት እንደተዘጋጀላቸው ተናግረዋል።

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ዋና ስራ-አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርዓያ ስላሴ በመግለጫው እንደገለፁት ሩጫው የምዝገባ ንቅንናቄውን ያግዛል ተብሎ የታመነበትና የፋይዳ ምዝገባን በህብረተሰቡ ውስጥ በስፋት ለማስረፅ በሌሎች ክልሎች ይህ የስፖርት ንቅናቄ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

አቶ ዮዳሄ የፋይዳ ምዝገባ እንደ ሃገር ጅማሮው መልካም የሚባል ቢሆንም በስፋት ከመመዝገብ አኳያ አሁንም የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ አክለዋል።

በፋይዳ ምዝገባ ላይ ያለውን የህብረተሰብ ግንዛቤ እና አረዳድ በስፖርት ንቅናቄ ማጠናከረ በእጅጉ አስፈላጊ በመሆኑ የተዘጋጀ የጎዳና ላይ ሩጫ መሆኑን የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አዮናስ አለማየሁ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ5ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ እንዳደረጉ አቶ ዮናስ ተናግረው በቀጣይ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም የከተማው ነዋሪ የፋይዳ መታወቂያ እንዲኖረው እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

142Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 140 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.