ከ25ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ከ25ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ፋይዳ ለኢትዮጵያ 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተጠናቀቀ።

ከ25ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ፋይዳ ለኢትዮጵያ 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተጠናቀቀ።

ግንቦት 03 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ከ25ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ፋይዳ ለኢትዮጵያ 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተጠናቀቀ።

በወንዶች አትሌት ይስማው ድሉ ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ይበልጣል በጋሻው እና ንብረት ክንዴ ተከታትለው ገብተዋል።

በሴቶች አትሌት ዮርዳኖስ ጽጋቡ አንደኛ፣ ንግስቲ ሞላ ሁለተኛ ይርጋለም ኪዳኔ ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ አትሌቶች የገንዘብ እና የሜዳልያ ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዶች ተበርክቷላቸዋል።

መነሻውና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ፋይዳ ለኢትዮጵያ 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እየተካሄደ ይገኛል።

ሩጫውን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በከተማ አስተዳደሩ ከ5ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች የፋይዳ ምዝገባ ማካሄዳቸውን ተናግረዋል።

የፋይዳ መታወቂያ የድጅታል ኢትዮጵያ ማሳያ እና የዘመናዊነት መገለጫ በመሆኑ ሁሉም የከተማው ነዋሪ እንዲመዘገብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሲቨል ምዝገባ እና የነዋሪዋች አገልግሎት ኤጀንሲ እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕርግራም ፅ/ቤት ሩጫውን በጋራ እንዳዘጋጁት ተመላክቷል።

+3

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

79Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 77 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.