
ቋሚ ኮሚቴው የቢሮውን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ።
ቋሚ ኮሚቴው የቢሮውን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ።
ግንቦት 7 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ማህበራዊ ጉዳይ ቆሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር አቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ገመገመ።
ቢሮው አካል ብቃት እንቅስቃሴ ባህል እንዲሆን በውድድርና በወጣቱን የአመለካከት ቀረጻ የሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሶፊያ አለሙ ሞዴል ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የማስፋፋት ስራ እንዲጠናከር አሳስበዋል
የቋሚ ኮሚቴው ድጋፍና ክትትል በቢሮው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አዋንታዊ ተጽእኖ ማሳረፍ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ አቶ በላይ ደጀን የስፖርት ማዘውተሪያ ከማስፋፋት እና የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን አመልክተዋል ላይ ገለጻ አድርገዋል
የ2017 የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ላይ ገለጻ ያደረጉት የዕቅድ በጀት ድጋፍ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አበባየሁ ዋና ዋና ተግባራትን ለማስፈጸም የተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቸውን አስገንዝበዋል፡፡
የከተማውን ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የስፖርት ልማት እቅዱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የተከናወኑ ተግባራት ሊጠናከር እንደሚገባ ያመላከቱት የቋሚ ኮሚቴ አበላቱ ከተማ አስዳደሩን በስፖርት ቀዳሚ ለማድረግ ወጣቶችን ለማነጽ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
60Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 58 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.