
የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራቸው በዘመናዊ መልክ እና በተሻለ የጥራት ደረጃ እየተገነቡ ነው/ አቶ በላይ ደጀን/
የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራቸው በዘመናዊ መልክ እና በተሻለ የጥራት ደረጃ እየተገነቡ ነው/ አቶ በላይ ደጀን/
ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በከተማ አስተዳደሩ እየተገነቡ የሚገኙ የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራዎች በዘመናዊ እና ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ እየገነቡ እንደሚገኝ ገለጹ
የከተማችን ወጣቶች በአካላቸው እንዲዳብሩ እና በአእምሯቸው እንዲበለጽጉ የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በኮሪደር ልማት እና በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተገነቡ የሚገኙ ማዘውተርያ ስፍራ ለከተማ ስፖርት እድገት ጉልህ ሚና እንዳላቸው አውስተዋል
ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ስፍራ እጥረት እንደነበረ ያስታወሱት አቶ በላይ ከተማ ከለውጡ ወዲህ ለስፖርት ስፍራዎች በሰጠው ልዩ ትኩረት ከ1400 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በሁሉም አከባቢ መገንባታቸውን ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ ለማዘውተርያ ስፍራ ትልቅ እድል ይዞ መምጣቱን ያወሱት አቶ በላይ ግንባታቸው በአጭር ጊዜ እና በጥራት እየተጠናቀቁ የሚገኙ ሜዳዎችን ሕዝቡ በባለቤትነት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል
ማዘውተርያ ስፍራቸው በአማካኝ በየመኖርያ አካባቢዎች በተሻለ ደረጃ መገንባታቸውን የገለጹት አቶ በላይ ለስፓርቱ እድገት እና ወጣቶችን ለማነጽ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል
ታዳጊዎችን በብቃት እና በጥራት ለማፍራት በከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየስራ እንደሚገኝ የገለጹት ቢሮ ኃላፊው የተገነቡ የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራዎች ደረጃቸውን ጠብቀው እየተገነቡ እንደሚገኝ ገልጸዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
151Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 149 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.