ወጣቶች በሥነ-ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ የወጣት...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ወጣቶች በሥነ-ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የጎላ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ

ወጣቶች በሥነ-ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የጎላ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ

ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ወጣቶች በሥነ-ምግባር እንዲታነጹ ብቁ እና ጤናማ እንዲሆኑ የጎላ ሚና እንዳላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ገለጹ

ቢሮ ማዕከላቱ ለወጣቶች ምቹ እና ማራኪ እንዲሆኑ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ያስታወቁት አቶ በላይ ቅጥር ግቢውን ከማስዋብ ባለፈ በአገልግሎት ለሚጠቀሙ ወጣቶች ልዩ ልዩ ስፓርታዊ እንቅስቃሴ የሚከወንበት ፣የትርኢት ሥራዎች እና የሥነ-ጽሑፍ ምሽት ለማካሄድ እንዲያስችሉ አውስተዋል

ማዕከላቱ የሚሰጡት አገልግሎት ከወጣቱ ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም በግብአት የማሟላት ተግባር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ በላይ አረጋግጠዋል

በከተማ አሰተዳደሩ ከ114 በላይ የወጣት ስዕብና መገንቢያ ማዕከላት መኖራቸውን ያወሱት አቶ በላይ በዝቅተኛ ስታንዳርድ የሚገኙትን ወደ መካከለኛ ለማምጣት በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል

ማዕከላቱ ወጣቶች ያላቸውን ተስጥኦ የሚያሳድጉበት እና ስብዕናቸዉን የሚገነቡበት ምቹ እና ማራኪ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ በላይ አመልክተዋል

በሥነ-ምግባር የታንጸጹ እና የነገዋን ኢትዮጵያ እንዲረከቡ በየደረጃው የሚገኙ የወጣት አመራሮች ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው የገለጹት አቶ በላይ የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

??👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

89አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 88 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.