ቢሮው ለወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የግብዓ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ቢሮው ለወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የግብዓት ድጋፍ አደረገ

ቢሮው ለወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የግብዓት ድጋፍ አደረገ

ግንቦት 15 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርትን ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ለወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት አገልግሎት የሚውል ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚገመት የግብዓት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የሰጡት የቢሮው ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ለወጣቱ ምቹ፣ ዘመናዊና ሳቢ ለማድረግ ማዕከላቱን በግብዓት ማሟላት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማ አስተዳደሩ 114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እንዳሉ የተናገሩት አቶ በላይ የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ኤና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ማዕከላት አስተዋፅኦቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

አቶ በላይ አያይዘውም ወጣቶች ለአገር በሚጠቅም ጉዳይ የሚመክሩበት እና የሚታነጹቡት ማዕከላንትን ደረጃውን በጠበቀ ቁሳቁሶች የማሟላት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል

ወጣቶች ያላቸውን ተሰጥኦ፣ ክህሎት እንዲያዳብሩ ማዕከላትን በግብአት ማሟላት ወሳኝ መሆኑን የገለጹት አቶ በላይ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የሚሰጡትን አገልግሎት ለማገዝ በዚህ ዓመት ብቻ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን አስታውሰዋል

ማዕከላቱ ወጣቶች ታለንታቸዉን የሚያሳድጉበት እና ስብዕናቸዉን የሚገነቡበት በመሆናቸው በተደራጀ የሰውኃይል እና ግብአት የማሟላት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

105You፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 103 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.