
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ ዜጎች የአምስት ሚሊየን ኮደሮች ኢንሼቲቭ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ።
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ ዜጎች የአምስት ሚሊየን ኮደሮች ኢንሼቲቭ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ።
ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የኢትዮጵያ መንግስት ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በ2026 አምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ የኮደሮች ኢንሼቲቭ ስራ በስፋት እየሰራ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የአምስት ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ስልጠና አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።
የአምስት ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ስልጠና ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በከተማዋ 218 ሺ በላይ ዜጎች ስልጠናውን መውሰድ እንደቻሉ የተናገሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በከተማዋ ካለው ምቹ ሁኔታ አንፃር ሲታይ ስራው በቂ አለመሆኑን ተናግረዋል።
ክቡር አቶ ጥራቱ አክለውም እንደ ሀገር ተወዳዳሪ ለመሆንና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ዜጎች የአምስት ሚሊየን ኮደሮች ኢንሼቲቭ እንዲቀላቀሉ በዚህ ወቅት ጥሪ አቅርበዋል።
ዜጎች የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ባለድርሻ ተቋማቱ በግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ላይ በስፋት በመስራት ዜጎች የተጨማሪ ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ መስራት ያስፈልጋል ተብሏል።
በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ143ሺ በላይ ዜጎች ስልጠና እንዲጀምሩ ተቋማቱ በቅንጅት እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የአምስት ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ በአራት የስልጠና ኮርሶች ማለትም በዌብ ፕሮግራሚንግ፤አንድሮይድ ፕሮግራሚንግ፤ ዳታ ሳይንስ እና ሰውሰራሽ አስተውሎት(AI) ዋነኛ የትኩረት ነጥቦች መሆናቸውንና ዜጎች ስልጣናቸውን ተከታትለው ሲጨርሱ ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት ባለቤት እንደሚሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል።
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
71Dawit Dave፤ Belay Dejen እና 69 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.