
የወጣቶችን እና የስፖርት ቤተሰቦችን ጥያቄ ለመመለስ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ /አቶ በላይ ደጀን/ ግንቦት 27 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የወጣቶችን እና የስፖርት ቤተሰቦችን ጥያቄ ለመመለስ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ /አቶ በላይ ደጀን/
ግንቦት 27 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን የወጣቶችን እና የስፖርት ቤተሰቦችን ጥያቄ ለመመለስ የተጀመሩ ስራዎች በማጠናከር የተገልጋዮች እርካታ ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታወቁ፡፡
በቢሮቸው በርካታ የከተማው ተፅእኖ ፈጣሪ ወጣቶችን እና የስፖርት ቤተሰቦችን ተቀብለው ያነጋገሩት አቶ በላይ ቢሮው በቅርብ ቀን የገባበትን ህንፃ ለተገልጋዮች ውብ ፣ ጽዱ እና ለስራ ምቹ አከባቢን ለመፍጠር የእረፍት ቀናትን ጨምሮ በአመራሩ እና በሰራተኛው በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡
የቢሮው አመራሮች እና ባለሙያዎች በአዲሱ ቢሮ መደበኛ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ የተናገሩት የቢሮ ሀላፊው አገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ፣ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ለማድረግ በግብአት እና በሰው ኃይል የማሟላት ስራም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ብቁ እና ውጤታማ ስፖርተኛ ለማፍራት ቢሮው የሚያደርገውን ጥረት ወጣቶች እንዲደግፉ አቶ በላይ አሳስበዋል።
ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦችም አዲሱን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ለአገልግሎት ምቹ እና ፅዱ መሆኑን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ 5ኪሎ ከነበረበት ህንፃ ወደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ወደ ሚገኝበት ህንፃ መዘዋወሩ ይታወቃል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.