
ቢሮው ለአልቲየስ ሩጫና እርምጃ ውድድር ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተቸረው ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
ቢሮው ለአልቲየስ ሩጫና እርምጃ ውድድር ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተቸረው
ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
ለቤተሰብ ጤና እንሩጥ" በሚል መሪ ቃል ለተዘጋጀው የሩጫ እና የእርምጃ ውድድር የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከአልቲየስ ጂም እውቅና ተሰጠው
ስፖርቱን ከመንግስት ድጎማ በማላቀቅ ራሱን ችሎ እንዲንቀቀስ ለማድረግ እንዲህ አይነት ውድድሮች ወሳኝ መሆናቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የከተማችን ብሎም የኢትዮጵያን ስፖርት ለማሳደግ በትብብርና በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል
አልቲየስ ጂም ለቢሮው ለሰጠው እውቅና በቢሮ እና በራሴ ስም አመሰግናለሁ ያሉት አቶ በላይ እንደዚህ አይነት መድረኮች የኢትዮጵያን ስፓርት ፓሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያስችሉ ገልጸዋል
ቢሮው የሩጫና እርምጃ ውድድሩ እንዲሳካ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሽልማት ሲያንሰው ነው ያሉት የአልቲየስ ጂም መስራች እና ስራ አስኪያጅ ኢንስትራክተር ቸሩ ኩሳ የማሕበረሰብ ጤናን ለመጠበቅ የሚረዱ ስፓርታዊ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
??ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.