ቢሮው "ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብ...

image description
- ውስጥ supporter    0

ቢሮው "ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ሐሳብ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ ግንቦት 28 ቀን 2017ዓ.ም

ቢሮው "ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ሐሳብ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ ግንቦት 28 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቫንት ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ። ሲቪል ሰርቫንቱ በሀገረ መንግስት ግንባታ እና እንደ ሀገር ለተመዘገቡ ውጤቶች ያበረከተው አስተዋፅኦ ላይ ገለጻ ያደረጉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ አዱኛ የሲቪል ሰርቫንቱ አሁናዊ ሁኔታ ሰፊ ማብራርይያ ሰጥተዋል ለዘላቂ ልማትና መልካም አስተዳደር ሰራተኛው የማይተካ ሚና እንዳለው ያስገነዘቡት ወይዘሮ መቅደስ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ያላቸውን የማይተካ ሚና ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል ወይዘሮ መቅደስ አያይዘውም የወጣቶችን ማሕብራዊ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ የስፓርት ልማት ስራዎች ለማጠናከር ሲቪል ሰርቫንቱ ባለው አስተዋጽኦ ላይ ገለጻ አድርገዋል በውይይቱ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የተመዘገቡ ለውጦችና የሲቪል ሰርቫንቱ ሚና፤ የሲቪል ሰርቪሱ አሁናዊ ሁኔታ፤ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት ወይዘሮ መቅደስ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን መሰረት በማድረግ የተሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥል ገልጸዋል መንግስት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በየዘርፉ ባካሄደው ሁሉን አቀፍ የሪፎርም ሥራ አበረታች ለውጦች መመዝገባቸው የመድረኩ ተሳታፊዎች ያወሱ ሲሆን ለውጡን ለማፋጠን የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑም አረጋግጠዋል ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/ ኢሜል addissport2013@gmail.com

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.