15ኛው ከተማ አቀፍ የጤና ቡድኖች ስፖርታዊ ውድ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

15ኛው ከተማ አቀፍ የጤና ቡድኖች ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ

15ኛው ከተማ አቀፍ የጤና ቡድኖች ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ

በ1ኛ ዲቪዝዮን መቻል፣ በ2ኛ ዲቪዝዮን አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣በጤና ቡድኖች ሰሜን አዲስ አበባ ጤና ቡድን የውድድሩ ሻምፒዮና ሆነዋል

ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፓርት ለሁሉም ኮሚቴ ጋር ያዘጋጀው 15ኛው ከተማ አቀፍ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የጤና ቡድኖች እና የሚዲያ ተቋማት ዓመታዊ ውድድር በአበበ ቢቂላ ስቴድየም ፍጻሜውን አገኘ

97 ቡድኖችና ተቋማት በማሳተፍ ከጥር 04 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስቴድየም ሲጠናቀቅ የቢሮ አመራሮች እና የስፓርት ለሁሉም ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ጨምሮ የስፓርት አፍቃሪያን ተገኝተዋል

በስፓርት ለሁሉም ኮሚቴ ጋር ላለፉት ስድስት ወራት ሲካሄድ የቆየው 15ኛው ከተማ አቀፍ የተቋማትና የጤና ቡድኖች ውድድር ላይ በ1ኛ ዲቪዝዮን16 ቡድኖች በ2ኛ ዲቪዝዮን 28 ቡድኖች፣ በጤና ዲቪዝዮን 25 ቡድኖች መሳተፋቸውን የስፓርት ለሁሉም ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈለቀ ዋቄ ነግረውናል

ጠንካራ ፉክክር ያስተናገደው የአንደኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ውድድር መቻል ስፖርት ቡድን የውድድሩ ሻምፒዮና ሲሆን ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የብር ሜዳልያ ባለቤት ሆኗል

በ2ኛ ዲቪዝዮን ወንዶች አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለዋንጫ ያደረጉት ፍልሚያ በአቃቂ አሸናፊነት ተጠናቋል

ዳኞችን በፈተነው የጤና ቡድኖች ውድድር ፈረንሳይ ቤላ ጤና ቡድን ከ ሰሜን አዲስ አበባ ጤና ቡድን ያደረጉት የዋንጫ ጨዋታ በሰሜን አዲስ አበባ አሸናፊነት ተጠናቋል

አስር ቡድኖች በተሳተፉበት የሴቶች የቮሊ ቦል ውድድር የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የፐብሊክ ሰርቪስ አቻውም 2ለ0 በማሸነፍ የውድድሩ ሻምፒዮና መሆኑን አረጋግጧል።

18 ቡድኖች ጠንካራ ፋክክር ባደረጉበት የወንዶች ቮሊቦል ውድድር የአዲስ ቮሊቦል ጤና ስፖርት ማህበር ከስኬት ባንክ ጋር ያደረጉት ፍልሚያ በስኬት ባንክ የበላይነት ተጠናቋል

የውድድሩ ሻምፒዮና ቡድኖች ኮከብ አሰልጣኝ ኮከብ ተጫዋች ኮከብ ግብ አግቢዎዥ የዋንጫ ሽልማት ከመበርከቱ ባሻገር ለተሳታፊ ክለቦች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

??👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.