ቢሮው ለታዳጊ ፕሮጀክት አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ቢሮው ለታዳጊ ፕሮጀክት አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ሰጠ።

ቢሮው ለታዳጊ ፕሮጀክት አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ሰጠ።

ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በከተማው ለሚገኙ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ሰጥቷል።

ህፃናት ጥበቃ ደህንነት ዙሪያ እና በስልጠና ሪፖርት ዝግጅት ላይ ባተኮረው የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ላይ የስፖርት ትምህርት ስልጠና ማዕከላት ኃላፊዎች፣ የስልጠና ባለሙያዎች እና ክፍለ ከተማ የስፖርት ስልጠና ቡድን መሪዎች ተሳትፈውበታል።

ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት በታዳጊ ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሰሩ አሰልጣኞች እና የስፖርት ባለሙያዎች በየጊዜው የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎችን መስጠት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት የቢሮው የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ ናቸው።

ዓለም በደረሰበት ዘመናዊ የስፖርት ስልጠና ለመድረስና ተፎካካሪ እና ውጤታማ ስፖርተኛ ማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ጎሳዬ የስስልጠናው ዓላማ በስፖርት ሙያ ላይ እየሰሩ የሚገኙ አካላት አቅማቸውን ለማጎልበት ታስቦ መዘጋጀቱን አሳውቀዋል

ህፃናት ልዩ ትኩረትና ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ውጤታማ ትውልድ ማፍራት እንደሚቻል የገለጹት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የመጡት አቶ ኃይለሚካኤል ሁላችንም ለህፃናት መብትና ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት በህፃናት ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶች መከላከል እንችላለን ብለዋል

ወቅታዊ፣ጥራት እና ተአማኒነት ያለውና ውጤታማ ሪፓርት ማቅረብ ለስፓርቱ ሁለንተናዊ ዕድገት አስፈላጊ ነው ያሉት አንስትራክተር በላይነህ አይችሉህም ከሳምንታዊ ሪፓርት ዝግጅት እስከ ዓመታዊ አዘገጃጀት እንደየ ስፖርት ባህሪ አንጻር መሰራት እንዳለበት አመላክተዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.