"የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና! "

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

"የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና! "

ኢትዮጵያ በወጣቶች ላይ ያላትን ተስፋ እና እምነት ያመላከተ በሳል ውይይት ነው - ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና! "

ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የከተማችን ወጣቶች

በወቅታዊ ፣ ሀገራዊና ከተማዊ ጉዳዮች ላይ ከአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ ጋር በመወያየት የጋራ ግንዛቤ ፈጥረዋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የወጣቶችን ፍላጎቶች ይበልጥ ለማወቅ ፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ የወጣቶችን ጥያቄዎች ለመለየትና ተግባቦት ፈጥሮ በቀጣዩ በጀት ዓመትም በጋራ ለመረባረብ የሚያግዝ መድረክ መሆኑን አመላክተዋል።

ወጣቶች የሀገር ኩራት ፣ የሀገር ተስፋዎችና የሀገር ጉልበት መሆናቸውን የጠቀሱት ክብርት ከንቲባ ነገሮችን ከራስ አኳያ ብቻ ሳይሆን ከሀገርና ከህዝብ ጥቅም አንፃር መመልከት እየተሻሻለ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የመበልፀግ ህልም የሚሳካው በወጣቶች መሆኑንና ጥቅሙም ከማንም በላይ ለሀገር ተረካቢ ወጣቶች መሆኑን ያስረዱት ክብርት ከንቲባ በወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ ለሀገራችን መስዋዕት ለመክፈል ጭምር ከወሰኑትና በአሻጋሪ እይታቸው ኢትዮጵያን ከጉስቁልና እያወጡ ወደ ከፍታ እያሸጋገሯት የሚገኙትን ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድን አርአያ ሊያደርጓቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በከተማችን የልማት እንቅስቃሴዎች ሁሉ ወጣቶች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና ወጣቶችም በሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፣ በሰላም ሰራዊት እንዲሁም በእያንዳንዱ የከተማችን የልማት ስራዎች ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ከወጣቶች ጋር የተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ በወጣቶች ላይ ያላትን ተስፋ እና እምነት ያመላከተ መሆኑን የጠቀሱት ክብርት ከንቲባ የኢትዮጵያን መልክ የምትመስል ፣ የኢትዮጵያን ብልፅግና የምትገልፅ ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ ውብ ከተማ ለመገንባት እየተደረገ ባለው ርብርብ ሚናቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የወጣቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከአመለካከት ቀረፃው ጀምሮ እየተደረገ በሚገኘው ርብርብ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል።

በከተማችን ከሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያዎች ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተሰሩ መሆናቸውን የገለፁት አቶ በላይ አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍም መተዳደሪያ ደንብ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

የከተማችን ወጣቶች በውይይት የሚያምኑ ስለሆኑ የከተማችን ሰላም ከማረጋገጥ ባሻገር ለሰለጠነ የፖለቲካ ባህል ግንባታም የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ትውልድ ግንባታ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ጎልተው የሚታዩ መሆናቸውን የጠቀሱት የውይይቱ ተሳታፊዎች በተለይም ለወጣቶች ስብዕና መገንቢያ እና መዝናኛ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ወጣቶች ትርፍ ጊዜአቸውን በአልባሌ ቦታዎች እንዳያሳልፉ አስችለዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ የወጣቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከምዝገባ ጀምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር የተቀናጀ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ዓመት ብቻ 301 ሺህ ለሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልፀዋል።

ከተማችን የልማት ማዕከልነቷ እንዲጠናከር እንጅ የሁከት ማዕከል እንድትሆን አንፈቅድም ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ጭምር ለርካሽ ፖለቲካ ማራመጃነት ለማዋል በሬወለደ ወሬ የሚያራምዱ አሉባልተኞች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤትነትን ለማረጋገጥ በክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የተጀመረውን ጥረት በሙሉ አቅማቸው እንደሚደግፉም የውይይቱ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.