በ6ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የሚሳተፈው የአዲስ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በ6ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የሚሳተፈው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ልዑክ ሽኝት ተደረገለት።

በ6ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የሚሳተፈው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ልዑክ ሽኝት ተደረገለት።

ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በ6ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የሚሳተፈው የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ልዑክ ሽኚት ተደረገለት።

አዲስ አበባን በመወከል የሚወዳደሩ የስፓርት ልዑካን የመላው ነዋሪና የስፓርት አፍቃሪያንን አደራ ይዘው እንደሚጓዙ የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ስፓተኞች ውድድሩን በበላይነት ከማሸነፍ ባሻገር የከተማ አስተደሩን ብራንድ የማስተዋውቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል

በቅርቡ በአገር አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ውድድሮች ውጤታማ ብንሆንም የስፓርት ማዕከል ለሆነው ከተማ አስተዳደር በቂ አይደለም ያሉት አቶ በላይ ስፖርተኞች በልምድ ያገኙት ክህሎት በሜዳ ላይ በማዋል የላቀ ብቃት በማሳየት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርበዋል

በውድድሩ ሁሉም ልዑካን በስፓርታዊ ጨዋነት በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መንፈስ እንዲያካሄዱ ያሳሰቡት አቶ በላይ የአዲስ አበባ አምባሳደር ሆነው የሚጓዙ ልዑካን የተሰጣቸውን አደራ በአሸናፊነት ሥነ ልቦና እንዲያጠናቅቁ አሳስበዋል

ከዘጠኝ ዓመት ቆይታ በሆላ በሚካሄደው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ በወጣቶች ኦሎምፒ ያገኘችውን ድል ለመድገም ሁሉም ስፓርተኛ ትልቅ ኃላፊነት አለበት ያሉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በአገር ውስጥ ትልቁ ውድድርን ውጤታማ ሆኖ ለማጠናቀቅ አብሮነት ወሳኝ መሆኑም አስገንዝበዋል

ስፖርት ለህብር ኢትዮጵያ አርበኝነት”በሚል መሪ ቃል ጂማ ከተማ በሚካሄደው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ26 የስፖርት አይነቶች ከ700 በላይ የስፓርተኞችን እንደሚያሳትፍ ተመልክቷል

በተያያዘ ዜና ለስፓርት ልዑካኑ በስፓርት ዲሲፕሊን እና በስፓርት ሳይኮሎጂ ላይ የሚያተኩር ስልጠና ለልዑክ የተሰጠ ሲሆን ለአዲስ አበባ የሚመጥን ሥነ ምግባር እና የሥነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል

የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ውድድር ከሰኔ 10 እስከ 19 2017 ዓ/ም በጂማ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

??👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.