የአገራችን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ለማድረግ ተስፋ የ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአገራችን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ለማድረግ ተስፋ የተጣለባቸው ሴት ዋናተኞች

የአገራችን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ለማድረግ ተስፋ የተጣለባቸው ሴት ዋናተኞች

ወደ ዋና ስፖርት የገባችው በ11 ዓመቷ በልዩ ስልጠና መርሃ ግር ነው፡፡ ተወልዳ ባደገችበት የአዲስ አበባ ቦሌ ቦራ የህፃናት መጫወቻ አካባቢ ባህር ባይኖርም በአንድ ታክሲ ሽው ብላ የምትሄድት ቀበና ውሃ ለዋና ብትነጥፍም የሩቅ ሕልሟን ለማሳካት አንድ መንገድን ተከትላለች ስልጠና! የሚሰጠኝን ስልጠና በብቃት ከተወጣው አገሬን አስጠራለሁ የሚል እምነት ይዛ አንድ ብላ የጀመረቸው ልምምድ በአንድ ዓመት 20 የወርቅ ሜዳልያ ለከተማዋ በማምጣት ስሟን በደማቁ የጻፈች ለዓለም አቀፍ ውድድር እየታተረች ምተገኝ አመለ ሸጋዋ የ15 ዓመት ልጅ በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ደምቃ ታይታለች

ሳምራዊት ደምሴ በወላይታ ሶዳ ከተማ አዘጋጅነት በተካሄደው የታዳጊዎች ምዘና ውድድር ላይ ነው ፍሬዋ መታየት የጀመረው ፤ በአሸናፊነት የታነጸቸው ታዳጊ የድል ውጤቷ በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ተጨማሪ 10 የወርቅ ሜዳልያ በማስገባት ሕልሟን መኖር ጀምራለች፡፡ አባት እና አናቷ ከስፖርቱ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ባይኖራቸውም ፍላጎቷን ከማገዝ ወደ ኃላ ብለው አያውቁም ሳምራዊት በአንደበቷ ወላጆቼ ለእኔ ያላቸው ድጋፍ በቃላት የማይገለጽ ወደ ስኬቴ መግቢያ በር ናቸው ትላላች፡፡

በውሃ ዋና ድንቅ አቋሟን ያሳየችው ሳምራዊት በትምህርቷም ከኮከቦች ተርታ የምትመደብ፣በጸባይም የፊት መስመር የሚሰጣጥ፤ባለተሰጥኦው ታዳጊ በትንሽ ዕድሜዋ በሁለት የውድደር ዘርፍ 20 የወርቅ ሜዳልያ በማስመዝገብ ያልተመዘገበ ክብረወሰን ሰብራለች፡፡

አሰልጣኜ እስከዳር አቻምየለህ ልምምድ እንደላቋርጥ ይመክረኛል!አዋ የምፈልገው ቦታ እስክደርስ ከመማር ወደ ኋላ አልልም! ይሄ የዛሬ ትልቁ ደስታዬ ሲሆን ነገ በኦሎምፒክ አደባባይ አገሬን ማስጠራት ደግሞ ማሳካት የምፈልገው የደስታዬ ጥግ ነው ትላለች፡፡

በአንጸባራቂው የውሃ ዋና ድሏ ብዙ ጓደኞችዋን የማረከቸው ሳምራዊት በግል እና በቡድን ካሳከችው ክብረ ወሰን ባሻገር ከተማችን በስስት የሚያያት የነገ የኢትዮጵያ ፈርጥ እንደምትሆን ትልቅ ኃላፊነት በትንሽ ትከሸዋ የያዘች ሩቅ አላሚ ናት፡፡

እንደ ሳምራዊት ሁሉ በዘንድሮ ውድድር በወርቅ ከደመቁት መካከል ቤተልሄም አለኽኝ ተጠቃሽ ናት፡፡ 6 የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት በመሆን የነገን የውሃ ዋና ስፖርት ለመታደግ ተስፋ የተጣለባት ሌላኛዋ ሴት ዋነተኛ የቤት ሥራዎን ከወዲሁ ጀምራለች፡፡

የአራት ወርቅ ባለቤቷ ክርስቲያን አበበ አዲስ አበባ ካፈራቻቸው ምርጥ ዋናተኞች አንዷ ናት፡፡ በውሃ ዋና የስኬት ጉዞዋ አሰልጣኞች በስስት የሚያይዋት ክርስቲያን የልጅ አዋቂ በመሆን ልጅነቷን በስኬት የጀመረች የጥሩ ውጤት ባለቤት ናት

በውሃ ዋና ስማቸው ከፍ ያለውን ስፍራ ከያዘው ባህር ዳር፣ ኮሞቦልቻና ድሬደዋን የሚያስነቁ ክስተቶች አዲስ አበባ እያፈራች ትገኛለች፡፡በተለይ ሴት ዋናተኞች ለመላው ኢትዮጵያ የተዘጋጁ መላውን ወርቅ ወደ አዲስ አበባ በማስገባት ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በልዩ ስልጠና እየሰለጠኑ የሚገኙ ታዳጊዎች ዘንድሮ ፍሬያቸው ታይቷል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብ እያሰለጠናቸው ከሚገኙ ታጋዲ ወጣቶች በርካቶቹ ሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባታቸው ከተሰራ ውጤት ማምጣት እንደሚያስችል ማሳያ ነው፡፡

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.