
ከተማ አስተዳደሩ በስፔሻል ኦሎምፒክ እና በባህል ስፖርቶች አጠቃላይ አሸናፊ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነ
ከተማ አስተዳደሩ በስፔሻል ኦሎምፒክ እና በባህል ስፖርቶች አጠቃላይ አሸናፊ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነ
በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የተሳተፈው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ልዑክ በስፔሻል ኦሎምፒክ እና በባህል ስፖርቶች አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን የሁለት ዋንጫ ባለቤት ሆነ
በ6ኛ መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በሃያ ስድስት የስፓርት አይነት የተሳተፈው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ማጠናቀቁ ተመልክቷል
ከተማ አስተዳደሩ በባህል ስፖርቶች ውድድር በ5 ወርቅ በ5 ብር እና በ3 ነሐስ በማምጣት ውድድሩን በ1ኝነት ባማጠናቀቅ የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል
በስፔሻል ኦሎምፒክ በ8 ወርቅ በ10 ብር እና በ7 ነሐስ ያስመዘገበው የስፓርት ልዑኩ የውድድሩ ሻምፒዮና መሆኑን አረጋግጧል
በኦሎምፒክ እና ኦሎምፒክ ባልሆኑ ውድድሮች በአጠቃላይ ውጤት በ84 ወርቅ 64 ብር እና 70 ነሐስ በማምጣት ደማቅ ታሪክ መጻፍ መቻሉ ተመልክቷል
ተተኪ ስፓርተኞችን በብዛት እና በጥራት ለማፍራት የተደረገው ጥረት ውጤታማ መሆኑ በታየበት የቦክስ፣የሜዳ ቴኒስ ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በጠረፄዛ ቴኒስ፣ በጅምናስቲክ እና በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ስፖርቶች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንደኝነት አጠናቋል
በቼዝ ስፖርት ውድድር በ3 ወርቅ በ4 ብር እና በ1 ነሐስ ሲመዘገብ በዳርት ስፖርት ውድድር ውጤታማ መሆኑ ተመልክቷል
በዊልቸር ቅርጫት ኳስ በሁለቱም ፆታ የአዲስ አበባ ከተማ ሻምፒዮና መሆን ችሏል።
በፖራሊምፒክ ውድድርች በአጠቃላይ ውድድሮች 34 ወርቅ 24 ብር እና 25 ነሐስ ሲመዘገብ መስማት የተሳናቸው ውድድር በ7 ወርቅ በ7ብር እና በ7 ነሐስ በማምጣት የውድድሩ ምርጥ በመሆን አጠናቋል
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳደር በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ 84 ወርቅ ፣በ67 ብር እና በ70 ነሃስ ሜዳልያ ማስመዝገብ ተመልክቷል፡፡
ከ2008ዓ.ም ከተካሄደው 5ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ጋር ሲነጻጸር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሁን ያስመዘገበው አጠቃላይ ውጤት ከፍተኛ መሆኑን የስፓርት ማሕበራት ማደራጃና ውድድር ዳይሬክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል
ከተማ አስተዳደሩ ለስፖርቱ በሰጠው ልዩ ትኩረት በሁሉም የስፓርት መስክ ውጤታማ ተተኪዎች ማፍራት መቻሉ ተመልክቷል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
??ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.