
ቢሮው የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ አመራሮች ጋር ገመገመ።
ቢሮው የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ አመራሮች ጋር ገመገመ።
ሰኔ 26 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶቸና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኙ የወጣቶችና ስፖርት ፅ/ሀላፊዎች እና ከወጣት ስብዓና መገንቢያ ማዕከላት ስራአስኪያጆች ጋር ገመገመ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ቢሮው በበጀት አመቱ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የከተማዋን የስፖርት እድገት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
ለወጣቶችን የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ በተከታታይ በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ290ሺህ በላይ ወጣቶች በበጀት አመቱ የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው አቶ ደዊት ገልፀዋል።
ወጣቶች በከተማቸው ሁለንተናዊ ሰላም ላይ ቀጥተኛ ተሳትፍ እንዲያደርጉ በመደረጉ የአደባባይ በዓላትን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፋዊ፣ ሀጉራዊ እና ከተማዊ ሁነቶች ካለምንም ፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ የወጣቱ አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበረ ም/ቢሮ ሀላፊው አሳውቀዋል።
የህብረተሰቡ በተለይ የወጣቱ የዘወትር ጥያቄ የሆነውን የማዘውተሪያ ስፍራ እጥረት ለመቅረፈ በ2017 በጀት አመት ብቻ ከ122 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን መገንባት መቻሉን አቶ ዳዊት ገልፀዋል።
ለረጅም አመታት ተቆርጠው የቆዩ የፖሊስ፣ ዩኒቨርስቲ እና የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድሮች በበጀት አመቱ መጀመራቸው የህብረተሰቡን የስፖርት ተሳትፎ ከፍ ከማድረጉ በተጨማሪ ከተማ አስተዳደሩን በሀገር አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚወክሉ ስፖርተኞችን ማፍራት እንደተቻለ ም/ቢሮ ተናግረዋል።
የቢሮውን የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቶ ጌታቸው አበባየሁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዝርዝር አቅርበዋል።
የወጣቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከማይንድ ሴት ስልጠና ጀምሮ የተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በስፋት መሰጠታቸውን በሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል።
ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት፣ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ከመፍጠር እና ተወዳዳሪ እና ውጤታማ ስፖርተኛን ከማፍራት አኳያ በበጀት አመት የተሰሩ ሰራዎች በዝርዝር ቀርበዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አካላትም ቢሮው በበጀት አመቱ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ገልፀው በቀጣይ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አጠቃቀም ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት አለበት ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.