
ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ስፖርታዊ ፌስቲቫልና ውድድር ተካሄደ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ስፖርታዊ ፌስቲቫልና ውድድር ተካሄደ
ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የመጀመሪያው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ፌስቲቫልና ውድድር በሴቶች አደባባይ በድምቀት ተካሄደ
ለአካል ጉዳተኞች የተመቻቸ ከተማ በአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎ የበለጸገች አገር በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ውድድር መስማት በተስናቸው፣ በዊልቸር፣ ሙሉ በሙሉ አይን ሥውራን፣ጭላንጭል፣ እጅ ጉዳት እና በስፔሻል ኦሎምፒክ የሦስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሂዷል
አካል ጉዳተኞች በስፓርቱ በማሳተፍ የአገራችን ስንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው ማውለብለባቸውን ያስታወሱት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የተጀመረው ልማት አካል ጉዳተኞችን ያቀፈ መሆኑን ለማሳየት ይሄ ውድድር ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል
ስፓርታዊ ውድድሩ ለአካል ጉዳተኞች ትልቅ እውቅና የሚሰጥ ነው ያሉት የፖራሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንት አቶ በቀለ ጎንፋ መድረኩ ቀጣይነት እንዲኖረው በትኩረት እንደሚስራ ገልጸዋል
በአይን ስውራን ጭላንጭል ሴት
እናንት ተስፋዬ ፋሲካ አስናቀ የወርቅ እና የብር ሜዳልያ ሲያገኙ በዚሁ ካታጎሪ ወንዶች ባደረጉት ውድድር ዘልዓለም በበላይነት ሲያጠናቅቅ ተመስገን ሞላ እና አየንው እንግዳ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ወጥተዋል
ሙሉ በሙሉ አይነ ስውርን ወንድ
ሲሳይ መስፍን፣ይርዳኝ ድምስ፣እኔነው ካሳሁን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ሲወጡ ብቸኛዋ የሴት ተወዳዳሪ ማዕረጌ እየሩስ አሸናፊ ሆናለች
በዊልችር ወንድ ዳንኤል ሻምበል የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሲሆን ደምስ አበራ የብር እሱባለው ጋሻዬ የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሲሆኑ በሴቶች መካከል በተካሄዱው ውድድር አንቺነሽ ንብረት ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ አሹ አየለው እና
ጸሐይነሽ አማር 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል
መስማት የተሳናቸው ወንዶች ሐይማኖት መኳንንት አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ዘኪ አሳብ ሁሉተኛ ኢዮብ ሙሉቀን ሦስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፥ በዚሁ ካታጎሪ በሴቶች መካከል በተካሄደ ውድድር ፋሲካ ሃይማኖት ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ መድሃኒት ዎሊ ሁለተኛ አለም መዝገብ ሦስተኛ ሆና ውድድሩ ጨርሳለች
በአእምሮ እድገት ውስንነት ሴቶች ኤደን ተስፋዬ 1ኛ መስታወት ተስፋዬ 2ኛ፣ ዮርዳኖስ ከፈያለው3ኛ ስትሆን በወንዶች ሀብታሙ ወልዴ ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ታደሰ ጸጋዬ 2ኛ ሚሊዮን ያደታ 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል
እጅ ጉዳት ወንድ አምሃ ደምስ በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ ምትኩ ሂሩ እና
ገመቹ ኦቶላ ተከታትለው ገብተዋል
እጅ ጉዳት ሴት ብቸኛዋ አምሳለ ሃብተገብርኤል የወርቅ ሜዳልያ ተበርክቶላታል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ የአካል ጉዳተኞቸ ማህበር፣ መስማት የተሰናቸው ፌዴሬሽን እና ፓራሊምፒክሰ ኮሚቴ በጋራ ያዘጋጁት ስፖርታዊ ፌስቲቫል ላይ በየጉዳት አይነቱ ተሳትፈው አሸናፊ ለሆኑ ስፓርተኞች የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቷል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeb
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.