የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር 8ኛ መደበኛ ጠቅላ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።

ሰኔ 29 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአደዋ መታሰቢያ ሙዚየም አካሄደ።

በጉባኤው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የመደራጀት ዋና ግቡ በተበታተነ መንገድ ማሳካት የማንችለውን በቀላሉ ከግብ ለማድረስ ያስችለናል ብለዋል።

ወጣቶች ተደራጅተው መንቀሳቀሳቸው ለተጠቃሚነታቸው እና በሁሉም ዘርፍ ያላችውን ተሳትፎ ለማጎልበት ወሳኝ ነው ሲሉ ከቲባዋ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ወጣት ማህበር የከተማውን ወጣቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ማሕበሩ በከተማዋ ብሎም በሀገር ሁለንተናዊ ልማት እና ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ደማቅ አሻራውን ማስቀመጡን የገለፁት አቶ በላይ በቀጣይ ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል ብለዋል።

8ኛው የአዲስ አበባ የወጣቶች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የማህበሩን የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት አዳምጦ በሙሉ ድምፅ አፅድቆል።

ጉባኤው ለቀጣይ ሶስት አመታት የአዲስ አበባ ወጣት ማህበርን የሚመሩ የክፍለ ከተማ እና የከተማ አመራሮችን የመረጠ ሲሆን ወጣት በረከት ቢርቢሳን የማህበሩ ፕሬዘዳንት፣ ወጣት ፎሊ ንጉሴ ም/ፕሬዘዳንት፣ ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ ፀሀፊ እና ወጣት ተከስተ አያሌው ተቀዳሚ ም/ፕሬዘዳንት በማድረግ መርጧል ።

የማህበሩ ፕሬዘዳንት ሁኖ የተመረጠው ወጣት በረከት ቢርቢሳ በቀጣይ ለከተማው ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ከልብ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባኤው ማህበሩን ባለፋት ሶስት አመታት በስራ አስፈፃሚነት ሲያገለግሉ የቆዩ ወጣቶችን እውቅና በመስጠት አሰናብቶል።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.