
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር አቶ በላይ ደጀን ለማህበሩ ሁለንተናዊ እድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጠ።
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር አቶ በላይ ደጀን ለማህበሩ ሁለንተናዊ እድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጠ።
ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
አዲስ አበባ ከተማ ወጣት ማኅበር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የወጣቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዎጽኦ እውቅና ቸራቸው
በአድዋ ሙዚየም በተካሄደው የአዲስ አበባ ወጣት ማሕበር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው ለቢሮው ኃላፊው ዕውቅና የተሰጠው
ማኅበሩ ለሰጣቸው እውቅና ምስጋና ያቀረቡት አቶ በላይ የወጣቶችን ማህብራዊ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከማኅበሩ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል
አቶ በላይ አያይዘውም ወጣቶች በማስተባበር በአረንጓዴ አሻራ በጎ ፈቃድ በስራ እድል ፈጠራ የአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት፣የደም ልገሳ እና በሌሎች ማህበራዊ መስኮች ማኅበሩ ለሚያደርገው ሥራ ቢሮው እገዛ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል
ለአቶ በላይ ደጀን የተሰጠው ምስጋና የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዲሁም ገባኤው ከወረዳ ጀምሮ ሲካሄድ ቢሮው ላደረገው ድጋፍ መሆኑ ተመልክቷል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.