
"የከተማ አስተዳደሩ ቀዳሚ አጀንዳው ህፃናት በአዕምሮና በአካል ጎልብተው እንዲያድጉ መንከባከብና ለዜጎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢን መፍጠር ነው" አቶ ጃንጥራር አባይነ
"የከተማ አስተዳደሩ ቀዳሚ አጀንዳው ህፃናት በአዕምሮና በአካል ጎልብተው እንዲያድጉ መንከባከብና ለዜጎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢን መፍጠር ነው" አቶ ጃንጥራር አባይነ
ሐምሌ 01 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን መርቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት አደረጉ።
እንደ አዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት ብቻ ወጣቶችና ህፃናትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 122 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች 1155 የህፃናት መዋያ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል ብለዋል አቶ ጃንጥራር አባይ
ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶች የከተማ አስተዳደሩ ለዜጎች ያለውን ውግንና የሚያሳይ ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር እነዚህ ፕሮጀክቶች ለመጭው ትውልድ የሚተላለፉና የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በመሆናቸው ህብረተሰቡ እንደ ዓይኑ ብሌን ሊጠብቃቸው ይገባልም ብለዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ቀዳሚ አጀንዳው ህፃናትን ተንከባክቦ ማሳደግና ለዜጎች ምቹ የመኖሪያን አካባቢ መፍጠር ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው ዛሬ በከተማችን የተመረቁት የወጣቶችና የህፃናት መጫወቻና መዋያ ስፍራዎች ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል።
ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶች ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበላቸው ናቸው ያሉት ኃላፊው እንደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማም መርቀን ለህዝብ አገልግሎት ያዋልናቸው ፕሮጀክቶች የከተማ አስተዳደሩ የፕሮጀክት አካል በመሆናቸው ለዚህ ስኬት የተጉ አመራሮችና መላው ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹ በከተማ አስተዳደሩ ባሉ በሁሉም ወረዳዎች የሚገነቡ መሆናቸው ከተማዋ መሬትን ከግለሰብ ተጠቃሚነት ወደ ህዝብ እየቀየረች ያለች ከተማ ስለመሆኗ ማሳያ ናቸውም ብለዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አዲሱ ሻንቆ በበኩላቸው ከተማዋ በሚያስደምም ሁኔታ እየተጋች የአፍሪካ መዲናነቷን እያረጋገጠች መሆኗን ገልፀው ዛሬ የተመረቁት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እንደ ትልቅ ማሳያ ይወሰዳሉ ብለዋል።
እንደ ቂርቆስም በመንግስት ወጭ የተሸፈኑ የወጣቶች መዝናኛና የህፃናት መዋያ ፕሮጀክቶችን በክቡር ምክትል ከንቲባው በእቶ ጃንጥራር አባይ አማካኝነት አስመርቀን ለህዝብ ክፍት አድርገናልና የክፍለ ከተማችን ወጣቶችና ህፃናት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.