በየካ ክፍለ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ የስፖር...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በየካ ክፍለ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የህፃናት የቀን እንክብካኬ ማዕከላት፣ መጫዎቻ ቦታዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

በየካ ክፍለ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የህፃናት የቀን እንክብካኬ ማዕከላት፣ መጫዎቻ ቦታዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

ሐምሌ 01 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በክፍለ ከተማው በ2017 በጀት አመት ተገንብተው የተጠናቀቁ የስፖርት ማዘውተሪያና ጂምናዚየሞች፣እንዲሁም የህፃናት የቀን እንክብካኬ ማዕከላት፣መጫዎቻ ቦታዎች ተመርቀው በዛሬው እለት ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በምርቃት መርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ሳሙኤል፣ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ፣ የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላናን ጨምሮ የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎች፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የስፖርትቤተሰብ አባላት እንዲሁም ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እንደገለፁት አዲስ አበባ ከተማ ስሟና ግብሯ የተገናኘላት የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ከተማ ለማድረግ ብርቱ አመራር በመስጠት ብርቱውን የከተማዋን ነዋሪ በማሳተፍ ከፍ ያሉ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

አቶ ሞገስ ባልቻ አክለውም በዛሬው እለት በከተማዋ ተገንብተው የተጠናቀቁ 122 የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና 1155 በቀዳማይ ልጅነት መርሀ ግብር የተከናወኑ የህፃናት የቀን እንክብካኬ ማዕከላት፣መጫዎቻ ቦታዎች በጥቅሉ 1277 ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ገልፀዋው እነዚህ ብዙ ካፒታል የፈሰሰባቸውን ፕሮጀክቶች ህብረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው አስተዳደሩ በ2017 በጀት አመት በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በመንግስት ካፒታል ችግር ፈቺ የሆኑ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተው በዛሬው እለት ግንባታቸው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ እና ግብአት የተሟላላቸው የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የህፃናት የቀን እንክብካኬ ማዕከላትና መጫዎቻ ቦታዎች እንደ ከተማ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ገልፀዋል።

የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ምርቃትን ተከትሎ ለታዳጊዎች የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ተበርክቷል።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.