
በክረምቱ የምናከናውነው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከሕብረተሰባችን ጎን መሆናችንን የምናሳይበት ትልቅ ዕድል ነው፡፡/አቶ በላይ ደጀን/
በክረምቱ የምናከናውነው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከሕብረተሰባችን ጎን መሆናችንን የምናሳይበት ትልቅ ዕድል ነው፡፡/አቶ በላይ ደጀን/
ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የምናከናውነው የአረንጓዴ አሻራ፣የአረጋውያን ቤት ዕድሳት፣ የደም ልገሳ፣ ሰብአዊ አገልግሎትን ጨምሮ አስረ አራቱ የስምሪት መስኮች ከሕብረተሰባችን ጎን መሆናችን የምናሳይበት መድረክ ነው ሲሉ ገለጹ
የህሊና እርካታ በመሆነው የበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች በንቃት እንዲሳተፉ የጠየቁት አቶ በላይ ተተኪው ትውልድ ነገ የሚረከቧት ኢትዮጵያን ጽዱ እና በንጽሑ አየር የተሞላች እንድትሆን ዛሬ የሚተክሉ ችግሩን ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል
አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ትልቅ ኃላፊነት የወጣቶች መሆኑን ያወሱት አቶ በላይ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማህበራዊ ኃላፊነታችን ለመወጣት የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል
ነገ ማለዳ በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደሚካሄድ አቶ በላይ ጠቁመዋል
በጎ ፍቃድ አገራዊ አንድነት እና ወንድማማችነት የመፍጠር ትልቅ አቅም እንዳለው የገለጹት አቶ በላይ በአገልግሎቱ በንቃት በመሳተፍ ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.