
ቢሮው #በመትከል_ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል 7ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካሄደ
ቢሮው #በመትከል_ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል 7ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካሄደ
ሐምሌ 08 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል የቢሮው ሰራተኞችን ጨምሮ የከተማው ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች የሚሳተፋበት የአረንጓዴ አሻራ የንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አካሄደ።
በንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚመጣውን መዘዝ ለማስቀረት አረንጓዴ አሻራ ማኖር አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው ብለዋል።
ችግኞችን ከመትከል ባለፈ ተንከባክቦ እንዲጸድቁ የማድረግ ስራ ሊጠናከር ይገባል ያሉት አቶ በላይ ወጣቶች ነገ የሚረከቧት ኢትዮጵያን ጽዱ እና በንጽሑ አየር የተሞላች እንድትሆን ዛሬ የምንተክላቸው ችግኞች ወሳኝ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እንደ ሀገር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በመዲናችን በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተነሳሽነት መጀመሩን ያስታወሱት አቶ በላይ ከለውጡ ወዲህ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀልበስ የተስሩ ሥራዎችን ውጤታማ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
ንጹህ አየር ጤናማ፣ንቁ፣ ብቁ ወጣትና ውጤታማ ለስፓርተኛ ለማፍራት ትልቅ ዋጋ እንዳለው የገለጹት አቶ በላይ አረንጓዴ አሻራ ማኖር ምቹ ቦታን ከመፍጠር ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።
በዛሬው የአረንጎዴ አሻራ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ከ4ሺህ በላይ ችግኞችን መትከል እንደተቻለ የገለፁት የቢሮው ሀላፊው በቀጣይ የወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች በየአከባቢያቸው የአረንጎዴ አሻራን ጨምሮ በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያካሂዱ አሳስበዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው ምርጥ ስፖርተኛ ለማፍራት ከታዳጊ ጀምሮ ማሰልጠን እንደሚገባ ሁሉ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን መከባከብ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማን የአረንጎዴ አሻራ መርሀ ግብር በሁሉም አከባቢዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ አቶ አድማሱ አሳውቀዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.