
ጤናዉ የተጠበቀ ፣ አካሉ የዳበረ አመራር ለምናልመዉ ብልፅግና ወሳኝ ነዉ።
ጤናዉ የተጠበቀ ፣ አካሉ የዳበረ አመራር ለምናልመዉ ብልፅግና ወሳኝ ነዉ።
መላዉ አመራራችን ከ2017 አመታዊ የስራ ግምገማችን እና እቅድ ዉይይት ጎን ለጎን የማስ ስፓርት አከናዉነናል ።
ዛሬ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማካሄድ ጀምረናል።
የ2017 በጀት ዓመት ከመቼውም የበለጠ ስኬት ያስመዘገብንበት ነው ፤ የእቅድ አፈፃፀማችን 95 በመቶ ተሳክቷል።
መዲናችንን ለሀገር ክብር የምትመጥን፣ እንደ ስሟ “ውብ አበባ" ለማድረግ በኮሪደር ልማት፣ በከተማ መልሶ ማልማት እና በወንዞች ዳርቻ ልማት ስራዎች፤ በስራ እድል ፈጠራ እና የገቢ እቅድን በማሳካትና ያገኘነውን ገቢ በቁጠባና ብክነትን በማስወገድ ለዘላቂ ልማትና ድህነት ቅነሳ በማዋል ዙሪያ በተከናወኑ ስራዎች አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል።
በሁሉም ስራዎቻችን ውስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ቀጣይነትን ያረጋገጥንበት፣ የበጀት ጉድለትን በህብረተሰብ ተሳትፎና በጐ አገልግሎት እየሞላን ከህዝብ ጋር ተቀራርበን በመስራት ውጤታማ የሆንበት በጀት ዓመት ነው።
ለነዚህ ሁሉ ስኬቶች አብራችሁን የለፋችሁ፣ ከራሳችሁ በላይ ህዝባችንን ያስቀደማችሁ የከተማችን ነዋሪዎች እና የደከማችሁና ውጤት ያስመዘገባችሁ አመራሮቻችንን እና ሰራተኞቻችንን ከልብ እናመሰግናችኋለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.