
ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ፬ " በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን ሲያከናወኑ የቆዩት ወሳን ተሻጋሪ በጎ ፍቃደኞች በአዲስ አበባ ከተማ ጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
በመትከል ማንሰራራት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ለማሳደግ የሚደረግ ትልቅ ስራ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የወጣቶች ንቅናቄ እና ግንዛቤ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጤናዬ ታምሩ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃደኞች ሁሉም ክልል ሲያካነወኑ ከቆት የበጎ ፍቃድ ስራዎች አንዱ ችግኝ ተከላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጠቀሜታ እንዳቸው ያወሱት አቶ ጤናዬ እንዲህ አይነት መድረኮች የወጣቱ ትዉልድ ተሳትፎና ተቃሚነት በማረጋገጥ ለሁለንተናዊ አብሮነትና መተሳሰብ እንደሚያጎላ ገልጸዋል።
ከሁሉም ክልሎችና ከሁለት ከተማ አስተዳድሮች የተዉጣጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ነገ በወደቁትን አንሱ በጎ አድራጎት ማህበር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ በትራፊክ አገልግሎት፣ በደም ልገሳ እና በልዩ ልዩ ሰብአዊ አገልግሎቶች እንደሚሳተፉ ከወጣቶች ግንዛቤና ንቅናቄ ዳይሮክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
??ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.