
የተቋሙ የ2017 የስራ አፈጻጸም ምዘና መካሄድ ጀመረ
የተቋሙ የ2017 የስራ አፈጻጸም ምዘና መካሄድ ጀመረ
ሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ የዳይሬክተሮች፣ የድጋፍ ስራ ሂደቶች እና የሁሉንም ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የበጀት ዓመቱ ምዘና መካሃድ ጀመረ
በምዘናው ኮር ዳይሬክተሮች፣ ደጋፊ ስራ ሂደቶችና የአስረ አንዱም ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤቶች እንደሚያልፉ የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ አዱኛ ገልጸዋል
ምዘናው አፈጸጸምን መሰረት ያደረገ መሆኑን ያወሱት ወይዘሮ መቅደስ ለዚህ ተብሎ በተዋቀረ ኮሚቴ በታማኝነት በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲካሄድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ምዘናው በእቅድ ዝግጅት ላይ በተደረገው ስምምነት መሰረት ምንያህል ተግባራቸውን አከናውነዋል የሚለውን መሰረት ያደረገ መሆኑን የገለጹት የዕቅድ በጀት ድጋፍ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አበባየሁ የተሻለ አፈጻጸም ያገኙ ተቋማትን የማበረታት ስራ እንደሚከናወን አመላክተዋል
ምዘናው በመጠይቁ መሰረት መረጃና ሰንድን በማየት ብቻ የሚከናወን መሆኑን ያወሱት አቶ ጌታቸው ለ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ሥራ ለመስራት መነሻ እንድሚሆን ገልጸዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.