
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የክረምት የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ስፖርት ፌስቲቫል አካሄደ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የክረምት የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ስፖርት ፌስቲቫል አካሄደ።
ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ የክረምት የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ስፖርት ፌስቲቫልን በዛሬው እለት አካሂዷል።
በፌስቲቫሉ ላይ የተገኙት የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ኒእመተላህ ከበደ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በበጀት ዓመቱ በከተማ ደረጃ በተደረገው ምዘና ሶስተኛ ደረጃ በመውጣቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ወይዘሮ ኒእመተላህ አክለውም በስነ-ምግባርና በስፖርት የዳበረ ትውልድ በመገንባት ሂደት የስፖርት ቤተሰቦች ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም አስረድተዋል።
ለበጀት ዓመቱ ውጤት መገኘትም የስፖርት ቤተሰቦች ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን አመላክተው፣ በሚከናወኑ ማናቸውም ተግባራት ላይ ተሳትፎአቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
የክፍለ ከተማው የወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሳሙኤል አበበ በበኩላቸው ክፍለ ከተማው ስፖርትን የህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ተግባር ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ሳሙኤል አክለውም የስፖርት ፌስቲቫሉ ህብረተሰቡ በአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በንቃት እንዲሳተፍ ከማበረታታቱም በላይ፣ በክፍለ ከተማው ውስጥ የማህበራዊ ትስስርንና የጋራ መግባባትን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና እንደነበረው ገልጸዋል፣በቀጣይም መሰል ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይም በየወሩ በተካሄዱ የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ላይ ለላቀ ተሳትፎ ላደረጉ ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት ተበርክቷል።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.