"ኢትዮጵያ ችላለች" በሚል መሪ ሀሳብ የታላቁ ህ...

image description
- ውስጥ supporter    0

"ኢትዮጵያ ችላለች" በሚል መሪ ሀሳብ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ ምዕራፍን በማስመልከት በየካ ክፍለ ከተማ የማስ ስፖርት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

"ኢትዮጵያ ችላለች" በሚል መሪ ሀሳብ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ ምዕራፍን በማስመልከት በየካ ክፍለ ከተማ የማስ ስፖርት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

20 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶቸና ስፖርት ቢሮ

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር "ኢትዮጵያ ችላለች" በሚል መሪ ሀሳብ የማስ ስፖርት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ ዶክተር ምስክር ነጋሽ እንደገለፁት በመንግስት እና በህዝብ ያላሰለሰ ጥረት 99 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማጠቃለያ ምዕራፍን በማስመልከት የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ መካሄዱን አንስተው በሀገራዊ አቅም በተገነባው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የየካ ሚና የላቀ ነበር ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ይፍሩ በበኩላቸው አባቶቻችን የባርነት አስተሳሰብን ደምና አጥንታቸውን መስዋዕት አድርገው ይችን ሀገር አስረክበውናል እኛም እንደ አባቶቻችን አትችሉም የተባልነውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ገንብተን ኢትዮጵያ እንደምትችል አሳይተናል ያሉ ሲሆን በዚህ የድል ስሜት ላይ ሆነን ይሄንን የማስ ስፖርት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስናካሂድ ጤናማ፣አምራች፣ውጤታማ ዜጋ ለመፍጠር በማለም ነው ብለዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት እንደገለፁት ኢትዮጵያ ችላለች ችላም ወደ መጨረሻው ማጠቃለያ ምዕራፍ ደርሳለች በዚህም ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ስፖርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እሱባለው መንደዶ በበኩላቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ እና ስፖርት ትጋት፣ልፉት ውጤት የሚገኝባቸው በመሆኑ የሚነጣጠሉ አይደሉም በማለት የማስ ስፖርቱ እንዲሳካ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ የከተማ፣የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣የክፍለ ከተማው የስፖርት ቤተሰቦች፣የሰርከት አባላት የተገኙ ሲሆን በመድረኩ የካ አመራሮች ከየካ ፖሊስ ጋር የእግር ኳስ ጨዋታ፣የየካ ክፍለ ከተማ ሴት አመራሮች ከወረዳ 6 ሴት አመራሮች ጋር ገመድ ጉተታ፣የሰርከስ ትርኢት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል።

የካ ኮሙኒኬሽን

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.