የአካል ጉዳተኞችን በስፖርት ተሳታፊነት እና ተ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአካል ጉዳተኞችን በስፖርት ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉም ባለድርሻ አካል ትብብርን ይጠይቃል

የአካል ጉዳተኞችን  በስፖርት ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉም ባለድርሻ አካል ትብብርን ይጠይቃል። አቶ ዳዊት ትርፋ 
ህዳር 14 ቀን  2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች  ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር  የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ የስፖርት  ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በሚመለከት ዛሬ  በፍሬድ ሽፕ ሆቴል የፖናል ውይይት አካሂዷል።
ፖናል ውይይቱ  የተዘጋጀው በሀገራችን ለ31ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአካል ጉዳተኞች ቀንን  እና ለ13 ጊዜ የሚካሄደውን ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው ውድድር እና ፌስቲቫልን ምክንያት በማድረግ ነው።
በፖናል ውይይቱ ላየ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶ አቶ ዳዊት ትርፋ የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው የሁሉም ባለድርሻ አካል ትብብር ሲታከልበት ነው ብለዋል።
አካል ጉዳተኛ መሆን ከስፖርት የሚያርቅ አለመሆኑን የተናገሩት  አቶ ዳዊት አካል ጉዳተኞችን ወደ ስፖርቱ በማምጣት እና ተሳታፊ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ሁሉም ማህበረሰብ ሊሰራው የሚገባ የቤት ስራ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በጋራ በመሆን 13 ኛውን ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል አስመልክተው  ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.