በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በሚደረገው አገር አቀፍ ንቅናቄ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩ ላይ በነቂስ ወጥተው እንደሚሳተፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን አስታወቁ

ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በሚደረገው አገር አቀፍ ንቅናቄ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች እንደ ሁልጊዜው አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ታሪክ የሚሰሩበት ልዩ ቀን ነው ብለዋል አቶ በላይ

ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የወጣቶች ተሳትፎ ውጤታማ መሆኑ ያስታወሱት አቶ በላይ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር የመንከባከብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 24 2017 ዓ/ም በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀልበስ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

??👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.