የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ለቀድሞ አመራሮች...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ለቀድሞ አመራሮች የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብር አካሄደ

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ለቀድሞ አመራሮች የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብር አካሄደ

ሐምሌ 26 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ማህበሩን ለረዥም ዓመታት በአመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩ ለቀድሞ አመራሮች የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብር አካሄደ

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የከተማው የወጣቶች በከተማቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲያደረጉ እና ተጠቃሚም እንዲሆኑ የቀድሞ የመህበሩ አመራሮች በርካታ ስራዎችን እንደሰሩ ተናግረዋል።

ማህበሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ተቋማዊ አሰራር እንዲኖረው የቀደመው አመራር የሰራቸው ስራዎች በጥንካሬ ከመጠቀሱ እንደሆኑ የገለፁት አቶ በላይ አዲሱ የማህበሩ አመራሮች ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በድክመት የሚታዩትን በማስተካከል ለአዲስ አበባ ወጣት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ወጣት በረከት ቢርቢሳ በበኩላቸው የቀድሞ የማህበሩ አመራሮች ማህበሩ ተቆማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ባላቸው ልምድ እና እውቀት ማህበሩን እንዲያግዙ ጠይቀዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በቀጠይ ለከተማው ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ትኩረት አድርጎ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ወጣት በረከት አሳውቀዋል።

በመጨረሻም ባለፉት አመታት የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበርን በአመራርነት ላገለገሉ አመራሮች የእውቅና የምስክር ወረቀት እና ሽልማት ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ተበርክቷላቸዋል።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.