የ90 ቀን ዕቅድ አካል የሆነው የአካል ብቃት እ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የ90 ቀን ዕቅድ አካል የሆነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በእንጦጦ አምባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።

የ90 ቀን ዕቅድ አካል የሆነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በእንጦጦ አምባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።

ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ90 ቀን እቅድ አካል የሆነ የማህበረሰብ አካል ብቃት ንቅናቄ በእንጦጦ አምባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካሄደ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና ትምህርት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት የስራ ኃላፊዎች አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በየትምህርት ቤቱ የተገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ መሆናቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በ90 ቀን ታቅደው እየተከናወኑ ከሚገኙ ተግባራት መካከል አንዱ የትምህርት ቤቶችን ማህበረሰብ በማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ማሳተፍ መሆኑን ገልጸዋል

ሰዎች በሚማሩበት አከባቢ ስፓርትን ማስፋፋት የኢትዮጵያ ስፓርት ፓሊሲ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ያወሱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማፋጠን እና በአእምሮ የበለጸ ትውልድ ለማፍራት ስፓርት ትልቅ መሳሪያ መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋማት በ90 ቀን ዕቅድ ውስጥ ስፓርትን አካተው መስራታቸው ለዘርፉ መነቃቃት አስተዋጽኦ እንዳለው ያወሱት አቶ ዳዊት የማስ ስፖርት ንቅናቄ እንዲስፋፋ ቢሮ እያካሄደ ያለውን ሙያዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.