
ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የቅንጅትና ትብብር ስራዎች የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና 2018 በጀት አመት እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።
ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የቅንጅትና ትብብር ስራዎች የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና 2018 በጀት አመት እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።
ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የቅንጅት እና ትብብር ስራዎች የእቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት አመት እቅድ ላይ ከተቋማት ጋር ውይይት አካሄደ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶቸና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ቢሮው በ2017 በጀት አመት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅትና በትብብር በመሰራቱ የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማዋን ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።
በበጀት አመቱ ከ250ሺህ በላይ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የገለፁት አቶ በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን እጥረት ለመቅረፍ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ 1530 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት አንዲሰጡ ክፍት መደረጋቸውን ተናግረዋል።
ወጣቶች በከተማቸው ልማት እና ሰላም ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ በመደረጋቸው የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮችን ጨምሮ በመዲናዋ የሚካሄዱ የአደባባይ በዓላት፣ ስብስባዎችና የተለያዩ ሁነቶች ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከወኑ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር አቶ በላይ አስታውሰዋል።
የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲሁም የከተማዋን የስፖርት ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ተግባር ባለመሆኑ ሁሉም አካል በእቅዱ አካቶና ትኩረት አድርጎ ሊሰራው እንደሚገባ የቢሮ ሀላፊው አሳስበዋል።
በ2017 በጀት አመት በቅንጅት እና በትብብር ስራውቻችን በጥንካሬ የፈፀምናቸውን ተግባራት ማስቀጠል በክፍተት የታዩትን በማረም በ2018 በጀት አመት ውጤታማ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ አቶ በላይ ገልፀዋል።
በመድረኩ በ2017 በጀት አመት በቅንጅት፣ ትብብር እና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመስራት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶቸና ስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት አመት በቅንጅትና ትብብር ለመስራት ከ18 ተቋማት ጋር ስምምነትም አድርጎል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.