ቢሮው በ2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የዘርፉ ተቋማት እውቅና ሽልማት አበረከተ ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ።
ቢሮው በ2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የዘርፉ ተቋማት እውቅና ሽልማት አበረከተ
ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የዘርፍ ተቋማት እና ባለሙያዎች እውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብር አካሄደ
ለተቋማት እና ለባለሙያዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ቢሮው በ2017 አፈጻጸም የተሻለ ዉጤት እንዲያስመዘገብ ሁሉም የተቋሙ መዋቅር ትልቅ ሚና እንደነበረዉ አስታውሰው በቀጣይም ስፖርትን ለማስፋፋት የወጣቱን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቅንጅት መሰራት ይገባል ብለዋል።
በአዲሱ በጀት ዓመት የስፖርት ልማቱን ለማፋጠን እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁጭት ልንሰራ ይገባል ያሉት አቶ በላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ደረጃቸውን ለማስጠበቅ ዝቅተኛ ያመጡ ተቋማት የላቀ ደረጃ ለማምጣት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል
በክፍለ ከተማ መካከል በተደረገው ምዘና ቦሌ ክፍለ ከተማ አንደኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የላፕቶፕ ተሸላሚ ሲሆን ልደታ እና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች እኩል ነጥብ በማምጣት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ የኮምፒዩተር ሲሸለሙ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሦስተኛ በመሆን የፕሪንተር ተሸላሚ ሆኗል
ኮር ዳይሬክተሮች መካከል በተደረገው ምዘና የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት 1ኛ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና 2ኛ የወጣቶች ግንዛቤ እና ንቅናቄ ዳይሮክቶሬት 3ኛ በመሆን ተሸልመዋል።
ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት ማዕከል በተደረገው ምዘና አራት ኪሎ አንደኛ፣ ራስ ኃይሉ ሁለተኛ ቴኒስ ሜዳ ሦስተኛ ሆነው በማጠናቀቃቸው በእውቅናው ተካተዋል።
በፌዴሬሽኖች በተካሄደው ምዘና ስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ኢንተርናማሽናል ቴኴንዶ እና ቦክስ ፌዴሬሽን 2ኛ እና 3ኛ በመሆን የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል
በደጋፊ ዳይሬክተሮች ፋይናንስ 1ኛ የሰው ሃብት ልማት 2ኛ ዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ እና ኮሙኒኬሽም 3ኛ መሆናቸው ታውቋል
በ2017 በተካሄደው ምዝናው ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ የቢሮ ቡድኖች፣ የሁሉም ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤቶች እና የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እውቅና እና ሽልማት እንደተበረከተላቸው ተመልክቷል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 

እናመሰግናለን


ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219


ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014


ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet


ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/


ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/


ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.