#በለውጡ_የተለወጠ_ወጣት የመጀመሪያው ከተማ አ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

#በለውጡ_የተለወጠ_ወጣት የመጀመሪያው ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል በልደታ ክፍለ ከተማ በድምቀት ተጀመረ።

#በለውጡ_የተለወጠ_ወጣት

የመጀመሪያው ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል በልደታ ክፍለ ከተማ በድምቀት ተጀመረ።

ነሐሴ 04 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

''በለውጡ የተለወጠ ወጣት'' በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያው ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል በልደታ ክፍለ ከተማ በድምቀት ተካሄደ።

በፌስቲቫሉ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶቸና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በ2017 በጀት አመት እንደከተማ ከተፈጠረው የስራ እድል 79 ፐርሰንቱ ወጣቶች እንደሆኑ የገለፁት አቶ በላይ ወጣቶች ከስራ ፈላጊነት ተላቀው ስራ ፈጠሪ እየሆኑ መምጣታቸውን አሳውቀዋል።

የህብረተሰቡን በተለይ የወጣቱን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ይገንባል ጥያቄ ለመመለስ ከተማ አስተዳደሩ በወሰደው ቁርጠኝነት ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ 1530 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን የቢሮው ሀላፊው ገልፀዋል።

የወጣቶችን ስብዕና ለመገንባት ምቹ፣ ዘመናዊ እና ከ18 በላይ አገልግሎቶችን የሚሰጡ 114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በከተማ አስተዳደሩ እንደሚገኙ የገለፁት አቶ በላይ ወጣቶች ትርፍ ጊዜያቸውን በወጣት ስብዕና መገንቢያ እንዲያሳልፉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በየአመቱ የሚዘጋጁ የወጣቶች ፌስቲቫል ፕሮግራሞች ወጣቶች ያላቸውን ችሎታ እና ተስዕጦ የሚያወጡበት እንዲሁም ልምድ የማለዋወጡበት በመሆኑ ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን አቶ በላይ በንግግራቸው አሳውቀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው ፍታዊ የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

ብቁ፣ ንቁ፣ ጤናማ እና አምራች ወጣቶችን ለማፍራት በየአከባቢው የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆናቸውን የገለፁት ወ/ሮ ልዕልቲ ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በአግባቡ እንዲጠቀሙባቸው አሳስበዋል።

የወጣቶች ፌስቲቫል በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚካሄድ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን ቀጣይ ኮልፌ ክፍለ ከተማ የአዘጋጅነት አርማውን ከልደታ ክፍለ ከተማ ተረክቧል ።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.