በቦሌ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች በስራ ፈጠራ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በቦሌ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች በስራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ማይንድሴት ስልጠና ተሰጠ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች በስራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ማይንድሴት ስልጠና ተሰጠ፡፡

ነሐሴ 01 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶቸና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በክፍለ ከተማው ለሚገኙ ከ1500 በላይ ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ የማይድሴት ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው ላይ የተጀኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መክብብ ወልደሃና በሀገር ሁለንተናዊ ግንባታ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው የኢትዮጵያ ብልፅግና ለማረጋገጥ ወጣቶች የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል።

በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ የማይድ ሴት ስልጠና መሰጠቱ ወጣቶችን ከሰራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ እንዲሁም ስራን ሳያማርጥ የሚሰራ ወጣት ለማፍራት በር የሚከፍት መሆኑን ተናግረዋል።

ቦሌ ክፍለ ከተማ ለከተከታታይ ሶስት አመታት ላስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት የወጣቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ወሳኝ እንደነበር የተናገሩት የክፍለ ከተማው የወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አንዶለም አሰፋ ወጣቶች በክፍለ ከተማው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ሥልጠናውን የኢንተርናሽናል ዩዝ ፌሎውሺፕ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶ/ር ናም ፕል ህዩን የሰጡት ሲሆን ሀገራቸው ደቡብ ኮሪያን የስልጣኔ ታሪክ እና የወጣቶች ተሳትፎ በምሳሌነት በማንሳት ያስረዱ ሲሆን መንግስት፣ ህዝብ በተለይ ወጣቱ ሀይል የስራ ባህላቸውን በመቀየርና ርብርብ በማድረግ ዛሬ ላለችበት የስልጣኔ ደረጃ መድረሶን ገልፀዋል።

“ከድህነት ለመውጣት ሩቅ አልሞ መሥራትና መትጋት ያስፈልጋል” ያሉት ዶ/ር ናም፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ያላቸውን አቅምና ጉልበት እንዲሁም ዕውቀት ለሀገራቸው ልማት ለማዋል ሥራን ሳይንቁ መሥራትና ራዕይ ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.