
በአካል እና በአእምሮ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህል ልናደርግ ይገባል።
በአካል እና በአእምሮ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህል ልናደርግ ይገባል። አቶ ዳዊት ትርፉ
ህዳር 13 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉን ጨምሮ የቢሮው አመራሮች በተገኙበት የማለዳ የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በየካ ክፍለ ከተማ ከተማ በሚገኝው ወንድይራድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።
በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ባስተላለፋት መልዕክት የአካል እና በአእምሮ የዳበረ ትውልድን ለማፍራት የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም በከተማው በሚገኙ መንግስታዊ እና የግል ትምህርት ቤቶች በሳምንት ሁለት ቀናት እንደሚካሄድ የተናገሩት አቶ ዳዊት በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.