የቦሌ ክፍለ ከተማ የክረምት የታዳጊዎች እግር ኳ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የቦሌ ክፍለ ከተማ የክረምት የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር ተጀመረ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ የክረምት የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር ተጀመረ።

ነሐሴ 04 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የቦሌ ክፍለ ከተማ የክረምት የታዳጊዎች የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ።

በውድድሩ መክፈቻ ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ ባደረጉት ንግግር ታዳጊዎች በስፖርታዊ እንቅስቃሴ በመሳተፍ ብቁ ስፖርተኞች እንዲሆኑ በስፋት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

"የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ጉልህ ጠቀሜታ አለው" ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ተወዳዳሪ ቡድኖች በስፖርታዊ ጨዋነትና ዲሲፕሊን ውድድራቸውን እንዲያካሂዱ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ለስፖርቱ ዕድገት ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን አውስተው፣ በቦሌ ክፍለ ከተማም በስፖርት መሠረተ ልማት ማስፋፋት እና በታዳጊዎች ስፖርት ሰፊ ሥራ መሠራቱን አመልክተዋል።

በውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚረዳ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል።

ውድድሩ በሦስት የዕድሜ ምድቦች እንደሚካሄድ ያስታወቁት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም አሰፋ፣ የ13፣15 እና 17 ዓመት በታች ቡድኖች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።

ቦሌ ኮሙኒኬሽን

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.