ቢሮው ከክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤቶች...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ቢሮው ከክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤቶች ጋር በ2018 በጀት አመት የልማት ዕቅድን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ተፈራረመ

ቢሮው ከክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤቶች ጋር በ2018 በጀት አመት የልማት ዕቅድን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ተፈራረመ

ነሐሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፍ ተቋማት የልማትን ዕቅድን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ፊርማ ተፈራረመ

የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ስፓርትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር እና የማዘዉተርያ ስፍራዎችን ለማልማት በጋራ ለመስራት በተደረገው ስምምነት ከ11ም ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት፣ከሁሉም ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት እና ከ114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ጋር መካሄዱ ተመልክቷል

ቢሮው ከ17 ሴክተር ተቋማት ጋር የውል ስምምነት መፈረሙን ያስታወሱት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ስምምነቱ በዘርፍ ተቋማት የሚሰሩ አመራሮችና ባለሙያዎች የወጣቱን ጉዳይ አብይ አጀንዳ በማድረግ እና ስፖርት ባህል እንዲሆን እየሰሩ ያሉትን ስራ ለማጠናከር እንደሚያስችል ገልጸዋል

አቶ በላይ አያይዘውም በአገር አቀፍ ብሎም በከተማ ደረጃ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በወጣት እና በስፖርት ዘርፍ የተመዘገቡ ለውጦች በማጽናት በቀጣይ በማህበራዊ፣ በአኪኖሚያዊ እና በፓለቲካው ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን የልማት ዕቅድ ላይ ተቀናጅቶ መስራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል

አሰራሩን ከማዕከል እስከ ወረዳ ማስፋት፣ የውል ስምምነት ማድረግ ውጤቱን እየገመገሙ መለካት በትኩረት እንደሚሰራ ያመላከቱት አቶ በላይ በዲሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር ስራዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

??👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.