በ2017 ባጀት አመት ተገንብተው ለአገልግሎት ክ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በ2017 ባጀት አመት ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ላይ ምልከታ ተደረገ።

በ2017 ባጀት አመት ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ላይ ምልከታ ተደረገ።

ነሐሴ 07 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በ2017 በጀት አመት ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉትን የኮልፌ መላጣ ሜዳን እና የአዲስ ከተማ ኒኮላ ሜዳን ተዘዋውረው ምልከታ አካሄዱ።

በየአካባቢው ተገንብተው ክፍት የተደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለታዳጊዎች፣ ለወጣቶች እና ለአከባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በምልከታቸው ማረጋገጣቸውን አቶ በላይ ገልፀዋል።

ሜዳዎችን በሀላፊነት ስሜት በጥንቃቄ እና በፍታሀዊነት መጠቀም እንደሚገባ የተናገሩት አቶ በላይ በተለይ ለታዳጊዎች እና ለወጣቶች ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በ2017 በጀት አመት ብቻ 122 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ያስታወሱት የቢሮ ሀላፊው ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ 1530 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ህብረተሰቡ እየተገለገለባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በሜዳዎች ላይ ሲጫወቱ ያገኝናቸው ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና የአከባቢው ነዋሪዎችም ሜዳዎቹ ዘመናዊ ተደርገው መሰራታቸው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት፣ ጤናቸውን ለመጠበቅና የረፍት ጊዚያቸውን አልባሌ ቦታ እንዳያሳልፉ እንደረዳቸው ተናግረዋል

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.