ቢሮው በዩኒሴፍ በጀት ድጋፍ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ማዕከል ሊያስገነባ መሆኑ ተገለጸ
ቢሮው በዩኒሴፍ በጀት ድጋፍ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ማዕከል ሊያስገነባ መሆኑ ተገለጸ
በቦሌ ክፍለ ወረዳ 1 ለሚገነባው ማዕከል የሳይት ርክክብ ዛሬ በይፋ ተካሂዷል ፡፡
ነሐሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ በጀት ድጋፍ በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 1 ሊገነባ የታቀደው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ማዕከል ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ በይፋ አካሄደ ፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት በስፋት እየተገነቡ እንደሚገኝ ያስታወሱት የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ኃይሌ ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ በክፍለ ከተማቸው ይህን መሰል ማዕከል ለመገንባት ላሳየው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል
የማአከሉ መገንባት በትውልድ ግንባታ እና ህፃናት ጤናማ ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት አቶ ፍጹም ስፖርተኞችና በፕሮጀክት የታቀፉ ታዳጊ ወጣቶችን ለማነጽ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል
ዩኒሴፍ ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ከልምድ በኃላ ምገባ እና በህይወት ክህሎት በጋራ ያከናወኗቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ያስታወሱት በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የስርአት ምግብ ኃላፊ ስታሊን ቺትክዊ ማሳያ የሆነውን የታዳጊዎች ማዕከል ግንባታ ለማስፋፋት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል
የማዕከሉ መገንባት በከተማ አስተዳደሩ ብቁና ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል ያወሱት ሚስተር ስታሊን ዩኒሴፍ ቢሮው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል
ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ90 ቀናት የንቅናቄ ተግባራት 60121 ታዳጊ ወጣቶችን በ25 የስፖርት አይነት ከ884 በላይ አሰልጣኞች በ824 የስልጠና ጣቢያዎች የስፖርት ስልጠና
በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 

እናመሰግናለን


ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219


ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014


ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet


ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/


ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/


ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.