
የማይንድ ሴት ስልጠና ለሁሉም የሞያ ዘረፍ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
የማይንድ ሴት ስልጠና ለሁሉም የሞያ ዘረፍ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዓለም አቀፉ ወጣቶች ሕብረት በምጽሐረ ቃል /IYF/ እና ከልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የሰጠው የማይንድ ሴት ስልጠና ለሁሉም የሞያ ዘርፍ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
የልደታ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍታለው ከፍያለሁ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ተስስር ያላቸው የኮርያ አሰልጣኞች እየተሰጠ የሚገኘው የአስተሳብ ቀረጻ ስልጠና ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸው ወጣቶች ለለውጥ ራሳቸው በማዘጋጀት ነገን የተሻለ ለማድርግ በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ድኽነትን ለማሽነፍ በሚደረገው ወሳኝ ትግል ወጣቱን አጋዥ ለማድረግ የማይንድ ሴት ስልጠና ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ፍታለው ወጣቶች በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያላቸውን አመለካከት እና አስተሳሰብ የመለወጥ ከፍተኛ አቅም የሚፈጥረውን ስልጠና በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የማይንድ ሴት ስልጠና ዓላማ በአስተሳሰቡ የተገነባ አከባቢውን እና አገሩን መቀየር የሚችል ወጣት ማፍራት ነው ያሉት የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክብረዓለም ደምሴ ወጣቱን ብቁ እና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የማይንድ ሴት ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
በወጣትነት ዘመን በርካታ አገር የሚጠቅሙ ስራዎች የሚከናወኑበት መሆኑን በመረዳት ለመለወጥ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ክብረዓለም እንችላለን የሚል አስተሳበብ በመላበስ ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ልምድ ተግባራዊ በማድረግ በሚፈጠሩ ስራ እድሎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል
የማይንድ ሴት ስልጠናውን የሰጡት የዓለም አቀፉ ወጣቶች ህብረት ዳይሬክተር ዶክተር ናም የማይንድ ሴት ስልጠና ለሁሉም ሞያ እና ዘረፍ ወሳኝ መሆኑን አውስተው ለውጥ ለማምጣት የወጣቱን አስተሳሰብ መቀየር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን ከተጠቀመች እና ያላትን በርካታ የሰው ኃይል በመጠቀም ከኮርያ የስራ ባህል ትምህርት ከተወሰደ በዓለም ቀዳሚ መሆን ትችላለቸ ያሉት ዶክተር ናም ኮርያ አመለካከት ላይ በመስራቷ በዓለም ስም ጥር ላኪ መሆኗን አስገንዝበዋል፡፡
መቀመጫውን ኮርያ ካደረገው IYF ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር እየተሰጠ የሚገኘው የማይንድ ሴት ስልጠና የተማሪዎች የእረፍ ጊዜ ጋር መሆኑ ወጣቶች የእረፍ ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ እንዳያሳልፉ ከፍተኛ እገዛ ያደረገ እንደሚገኝ የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት አሳውቋል፡፡
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.