የወጣቶች ምክር ቤት ለማቋቋም በተዘጋጀው ዕቅድ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የወጣቶች ምክር ቤት ለማቋቋም በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ ቅድመ ምስረታ ውይይት ተካሄደ

የወጣቶች ምክር ቤት ለማቋቋም በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ ቅድመ ምስረታ ውይይት ተካሄደ

ነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የወጣቶች ምክር ቤት ለማቋቋም በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ ቅድመ ምስረታ ውይይት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

የምክር ቤቱ ምስረታ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ መክብብ ወልደሃና የከተማችን ወጣቶች በአካባቢያቸው ብሎም በአገራቸው ልማት ላይ ለሚያደርጉት ተግባር የምክር ቤቱ መቋቋም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የከተማችን ወጣቶች ከሀገር አልፎ በአፍሪካና በዓለም ላይ እንደየተሰጥኦና አቅማቸው ጎልተው የሚወጡበትን አማራጮች ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን የማደላደል ስራ የሚያከናውን ምክር ቤት መሆኑን ያወሱት አቶ መክብብ ምክር በቱ በአጭር ጊዜ ተቋቁሞ ስራ እንዲጀመር ቢሮው አስፈላጊውም እገዛ እንደሚያደርግ አመላክተዋል፡፡

የወጣቶችን ምክር ለማቋቋም በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ ገለጻ ያደረጉት የወጣቶች ግንዛቤና ንቅናቄ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጤናዬ ታምሩ ምክር ቤቱ ሲቋቋም ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ፍትሃዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ማስቻል ዋነኛው ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶችን ለማሳተፍ እና ለማስጠቀም እንደ አገር በተሰሩ ስራዎች ታሪካዊ ዳረውን በስፋት የዳሰሱት አቶ ጤናዬ በከተማችን የሚገኙ የወጣት አደረጃጀቶችን በአንድ ማዕቀፍ በማሰባሰብና ኃይላቸውን በማቀናጀት መምራት የሚያስችል ጠንካራ የወጣቶች ምክር ቤት ማቋቋም ባለው ፈይዳ ላይ ሰፊ ማብራራያ ሰጥተዋል፡፡

ለወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚቋቋመው ምክር ቤት ውስጥ በበጎ ፈቃድ የተቋቋሙ ማህበራት፣የሲቪክ ተቋማት የሙያ ማህበራት እና በተለያዩ ዘርፎች የሚንቀሳቀሱ ክበባት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.