
#እንኳን_ደስ_አላችሁ_እንኳን_ደስ_አለን!!! ሀገርን በመወከል ሊብያ ቤንጋዚ ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር ላይ የተሳተፈው የአዲስ አበባ ልዑክ አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ።
ሀገርን በመወከል ሊብያ ቤንጋዚ ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር ላይ የተሳተፈው የአዲስ አበባ ልዑክ አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ።
ነሐሴ 10 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ኢትዮጵያን በመወከል በሊቢያ ቤንጋዚ በተዘጋጀው አለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር ላይ የተሳተፈው የአዲስ አበባ ከተማ የብስክሌት ልዑክ አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን ውድድሩን አጠናቆል።
ውድድሩ ከነሐሴ 7 እስከ 9 የተካሄደ ሲሆን በቡድን በተካሄደ ውድድር ኢትዮጵያ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ ሞሮኮና ግብፅ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በተመሳሳይ በግል ኢትዮጵያዊ አንደኛ እና ስስተኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ ሞሮኮ ሁለተኛ በመሆን ውድድሮን አጠናቃለች።
ሀገርን ወክሎ የተሳተፈው እና አጠቃላይ አሸናፊ የሆነው የአዲስ አበባ የብስክሌት ልዑክ የወርቅ ሜዳልያና የገንዘብ ሽልማት ከአወዳዳሪው አካል እንደተበረከተለት ልዑክ ቡድኑን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ተናግረዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.