በ90 ቀናት ታቅደው የተፈፀሙ ተግባራት ዙሪያ ግምገማ ተካሄደ። ነሐሴ 15 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በ90 ቀናት ታቅደው የተፈፀሙ ተግባራት ዙሪያ ግምገማ ተካሄደ። ነሐሴ 15 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ90 ቀናት ታቅደው የተፈፀሙ ተግባራት ዙሪያ ግምገማ አካሂዷል። የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል አባላት በ90 ቀናት አቅደው በሁለት ወር ከ15 ቀን ያከናወኗቸውን ተግባራት አፈፃፀም በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶችን ጨምሮ የቅድመ ዝግጅት ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የብልሹ አሰራር፣ የቅንጅት ስራ፣ የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት እንዲሁም የስፖርት ልማት ስራዎች ላይ በተሰሩ በርካታ ስራዎች ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ በቀረቡ ሪፖርቶች ተመላክቷል። ግምገማውን የመሩት አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ የቢሮው እስከአሁን ባለው የ90 ቀናት የእቅድ አፈፃፀም በጥሩ ደረጃ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በቀጣይ ቀሪ ቀናት የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አቶ በላይ አሳስበዋል።
ለከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በየአከባቢው የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና፣ የብዙሀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የልማት ስራዎች በቀጣይ ትኩረት ተደርጎባቸው መሰራት እንዳለባቸው የቢሮ ሀላፊው ገልፀዋል። ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/ ኢሜል addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.