
የአዘርባጃን አምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ ቦስካን አንጋፋውን የመቻል ስፖርት ክለብ ጎበኙ።
ሕዳር 18 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዘርባጃን አምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ አንጋፋውነሰ የመቻል ስፖርት ክለብ ጎበኙ።
በመቻል ስፖርት ክለብ በመገኘት ለአምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ ቦስካን አቀባበል ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የመከላከያ ስነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን እና የመቻል ስፖርት ክለብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ደረጀ መንግስቱ እንዲሁም የስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰይፉ ጌታሁን ናቸው።
የአንጋፋውን የመቻል ስፖርት ክለብ ታሪክ እና አሁን የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም ለሀገራችን ስፖርት እያበረከተ ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለአምባሳደሩ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም ስፖርተኞችን ፣ የክለቡን ሙዚየም እና ጂምናዚየም ጉብኝተዋል።
አምባሳደር ቦስካን የመቻል ስፖርት ክለብን በመጎብኘቴ ደስታ ተስምቶኛል በቀጣይ ከመቻል ጋር አብሮ በስፖርቱ ዘርፍ ለመስራት የአዘርባጃን መንግስት ዝግጁ ነው ብለዋል።
አምባሳደሩ በተጨማሪም በዛሬው እለት የተመለከትነው የአንጋፋው የስፖርት ክለቡ ታሪክ ለኛ ትልቅ ተሞክሮ ስለሚሆን በጋራ ለመስራት በመቻላችን የመቻል ስፖርት ክለብ አመራሮችን ማመስገን እንፈልጋለን ሲሉም ሃሳብ ሰጥተዋል።
የመከላከያ ሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የመቻል ስፖርት ክለብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለአምባሳደር ቦስካን የክለቡ አርማ የሆነውን የስፖርት ቱታ ስጦታ አበርክተውላቸዋል አምባሳደሩም የአዘርባጃንን ባህላዊ ስጦታ አብርክተዋል።
የመከላከያ ማርች ባንድ በመቻል ስፖርት ክለብ በመገኘት ለአምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ ቦስካን አቀባበል አድርጓል።
ዘገባው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ነው
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.